ለደንበኛ ንጉሥነት አብነቱ

0
76

በቻይና ጂያንግዚ ግዛት የሚገኝ የተራራ ላይ መዝናኛ ቦታ ወይም (ሪዞርት) በሚሊዬን የሚቆጠር ዶላር በማውጣት በኤሌክትሪክ የኃይል ምንጭነት የሚሰሩ በርካታ ተንቀሳቃሽ መውጫ መውረጃዎችን እያስገነባ መሆኑን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ባለፈው ሳምንት አስነብቧል::

በቻይና ቀደም ባሉ ዓመታት ተራሮች አናት ላይ ወጥቶ እየዟዟሩ ተፈጠሯዊ ውበትን መቃኘት አድካሚ ጉልበት ጨራሽ ሁነት ነበር፤ በቅርቡ ግን በቻይና መስራቃዊ ግዛት ጂንታይ ሊንሻን በተሰኘው ውብ ቀጣና 1500 ሜትር ከፍታ ላይ ለመድረስ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ ተንቀሳቃሽ መውጫ መውረጃ ተተክሎ ሥራ ሊጀምር መቃረቡ ነው ለንባብ የበቃው::

የተንቀሳቃሽ ተራራ መውጫ መውረጃው ስራ በ2022 እ.አ.አ የተጀመረ መሆኑን  ያስነበበው ድረ ገጹ ከአንድ ወር በኋላ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ነው የተገለፀው:: በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራው መውጫ  መውረጃ በቻይና የመጀመሪያ አለመሆኑን ያስነበበው ድረ ገጹ ሊንሻን ተራራ ላይ የተገጠመው ከቀደሙት ከተራራው ግርጌ እስከ አናት መጓጓዣው መለያ (ሴንሰር) የተገጠመለት እና በርካታ መሞች ካሏቸው መካከል አንዱ እና በውስብስብነቱ ልዩ እንደሚያደርገው ነው ለንባብ የበቃው::

በቻይና ዠይጂያንግ ግዛት 350 ሜትር ከፍታ ላለው ለታንዩ ተራራ የተገጠመው ተንቀሳቃሽ መውጫ መውረጃ በ2023 እ.አ.አ በቀዳሚነት የተተከለ ነበር:: ከዚያ ወዲህ ግን ከታንዩ ተራራ በኋላ በርካታ ተንቀሳቃሽ መውጫ መውረጃዎች መተከላቸውን ድረ ገጹ አስነብቧል::

ለድካም አቅላዩ የዘመነ መጓጓዣ ከተገልጋዮች በርካታ አስተያየቶች ተሰጥተዋል:: ከተሰነዘሩት  መካከልም ከፊሎቹ ለአረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ለማንኛውም ሰው እኩል እድል መስጠቱን በጠንካራ እና ተመራጭ ጐኑ ሲያወድሱ  ከፊሎቹ በእግር በመጓዝ ሊገኝ የሚችለውን ደስታ የሚያመክን ነው ሲሉ በነቀፌታ ማጣጣላቸውን የድረ ገጹ ጽሁፍ በማጠቃለያነት ለንባብ አብቅቶታል::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሚያዝያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here