የደንዲ ኃይቅ በኦሮሚያ ክልል፣ ምእራብ ሸዋ ከዋና መዲናዋ አዲስ አበባ ደቡብ ምእራብ አቅጣጫ 88 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው የሚገኘው:: በተሽከርካሪ ከአዲስ አበባ ወደ ቦሌ በሚወስደው አውራ ጐዳና ወደ ምእራብ አቅንቶ ግንደ በረት ከተማ አቅራቢያ በተተከለው አቅጣጫ ማመላከቻ መሰረት ተጉዞ ከደንዲ ከተማ በምስራቅ በኩል ጥቂት ኪሎ ሜትር ተጉዞ መድረስ ይቻላል::
የደንዲ ኃይቅ የክብደት ማንሻ (dumbbele) ወይም ከ “8” ቁጥር ቅርጽ ጋር ይመሳሰላል፤ አጠቃላይ ስፋት ስምንት ኪሎ ሜትር እጥፍ ተለክቷል:: ስፋቱ መካከል ላይ የሚጠብበት ደግሞ 220 ሜትር ብቻ ነው::
ደንዲ ኃይቅ ከከበበው አቀበት በዝናብ ወቅት በሚወርድ ፍሳሽ ይታደሳል መገኛ ከፍታው 2 ሺህ 836 ሜትር ወይም 9 ሺህ 305 “ማይል” ከመሬት ወለል በላይ ተለክቷል::
በኃይቁ ዙሪያ የሚገኘው ሜዳ አረንጓዴ መንጣፍ የለበሰ ነው:: በደንዲ ተራራ ጫፍ ኃይቁን እና ዙሪያውን መመልከት ለጐብኚዎች የሀሴት ምንጭ ነው::
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር የሚያዝያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም