በሰሜን ወሎ ዞን የዋድላ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለዋድላ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የግንባታ ጨረታ ለ017 ቀበሌ የእንስሳት ጤና ክሊኒክ ጥገና፣ ሎት2. የውሃ መስመር ዝርጋታ ለ011 ቀበሌ ቁርቁር ሶለላ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ትቤት፣ ለ017 ቀበሌ ቁራበሳ ደጋ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ኮን 01 ቀበሌ የዶጊት 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታና የውሀ መስመር ዝርጋታ፣ ሎት3. ስሚንቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላቸሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድና መረጃ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተሰጣቸው ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠኑ ብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ አቅራቢዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋድላ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ባዘጋጀው በጨረታ ስፔስፍኬሽን መሰረት ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
- የተዘጋጀውን እያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይኖርባችኋል፡፡ ተጫራቾች ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
- የግንባታው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይ ሲሆን፤ የሲሚንቶው ጨረታ ደግሞ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
- የግንባታው ጨረታ በ22ኛ ቀን ከቀኑ 8፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን፤ የሲሚንቶው ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግ/ን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፤ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሚሞላው ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የወሰዱትን ሙሉ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በተረጋገጠና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ሲፒኦ ወይም በመ/ቤቱ በመሂ 1 ገቢ የተደረገ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ፤ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም፡፡
- ተጫራቾች ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 20 01 39 41 መጠየቅ ይችላሉ ፡፡
የዋድላ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

