ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
47

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አገልግሉት የሚውሉ ጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪና ጎማ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ሀጋዊ ንግድ የ2018 ዓ.ም ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ የእቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 102 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከረበያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ፋ/ን/አ ዳይሮክቶሬት ቢሮ ቁጥር 107 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀናት ከረፋዱ 3፡00 ድረስ በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 3፡05 ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ቁጥር 107 በ16ኛው ቀን በ3፡30 ይከፈታል፡፡ ጨረታ በሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለ ጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 22 70 /058 226 21 77 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here