ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
43

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ ለኮንስትራክሽን ባለስልጣን ቢሮ ለ2018 ዓ/ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ በኢትዮዽያ በፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፐፐብሊክ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና የሰሜን ምዕራብ ሪጅን አስተዳደር ከተከራያቸው ህንፃ አመታዊ ለ10 የተለያየ ስፋት (የካሬ መጠን) ላላቸው ክፍሎች፣ የሽንት ቤቶች እና ኮሪደሮች ወይም በአጠቃላይ የሁሉም የካሬ መጠን ስፋት በድምሩ 830.5 ካሬ መጠን የጽዳት አገልግሎት ለጽዳት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ግዥ በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሽናፊ ድርጀቶች ጋር ውል በመያዝ ግዥውን ለመፈጸም (አመታዊ) ውል በመያዝ ግዥውን መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብረ ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ አመታዊ ለ10 የተለያየ ስፋት ላላቸው ክፍሎች እና የሽንት ቤት የጽዳት አገልግሎት ፣ለጽዳት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 27 እና 28 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫረቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ገንዘብ ወይም /የአገልግሎቱን የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2,000 (ሁለት ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በቢሮው ገንዘብ ያዥ ገቢ አድርገው ደረሰኝ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ ኦርጅናል በማለት የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ የስባሰባ አዳራሽ በ16ኛው ቀን ይከፈታል፡፡ ቅዳሜ፣ እሁድ እና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 3:30 ታሽጎ 4:00 ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በጨረታው ውስጥ ካለ ሲሞሉ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዶክመንት በተለያየ ፖስታ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸጉ ሁለት ፖስታዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ለይኖረው ይቻላል፡፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 30 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 50 00 /058 226 61 80 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ ለኮንስትራክሽን ባለስልጣን ቢሮ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here