የምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ለምዕ/ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ለደም ባንክ አገልግሎት የሚውል ግንባታ ደረጃ 5 ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) እና ደረጃቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ የባንክ ዋስትና ሲፒኦ /cash payment order/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በምዕ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በማሰራት ዋጋ ከሞሉት የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው በቀረበው ዝርዝር መሠረት (bill of quantity) በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት ከገንዘብ ያዥ ከግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 26 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን የቴክኒክ እና የፋይናንስ ብሎ በመለየት በተለያየ ፖስታ በማድረግ በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ምዕ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ31ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምዕ/ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ትብ/መምሪያ በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም ህዝባዊ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ቅናሽ ወይም Rebate ማሰቀመጥ ከፈለጉ በዋጋ መሙያው ማጠቃለያ ላይ በተቀመጠው መሰረት በፐርሰንት ማሰቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በምዕ/ጎጃም/ገንዘብ መምሪያ ስም ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 05 87 75 08 95 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ

