ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
35

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለደንብ ልብስ ተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚውል ረጅም ቆዳ ጫማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ) ሺህ ብር እና በላይ ስለሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዛው ዕቃ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሺን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለመለየት እንዲቻል በግልጽ ፅሁፍ ኢንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ማስታወቂው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ተከታታይ ቀናት በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 46 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ን/አስ ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 46 በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 46 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በመላክ ወይም በስል/ቁ/ 058 220 9373 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here