ጊዜያዊ የረዥም ጊዜ( የኮንትራት)  የቅጥር ማስታወቂያ

0
53

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች ባለው ክፍት የስራ መደብ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን ከሚያሟሉ ስራ ፈላጊዎች መካከል በጊዜያዊ የረዥም ጊዜ  (በኮንትራት) ቅጥር አወዳድሮ በመቅጠር ማሰራት ይፈልጋል፡፡

 

 

ተ.ቁ የሥራ መደቡ መጠሪያ ደረጃ የመ/መ/ቁ ደመወዝ ብዛት ዳይሬክቶሬት/ዝግጅት የሥራ ቦታ ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት ተፈላጊ የስራ ልምድ
1. የኦሮሚኛ ቋንቋ ሪፖርተር 1 VIII አሚ-732

አሚ-733

 

 

በኮርፖሬሽኑ የደመወዝ ስኬል መሠረት 02 ኦሮሚኛ ዝግጅት ባ/ዳር በብሮድካስት ጋዜጠኝነት፣ በጋዜጠኝነትና ተግባቦት፣ በተግባቦት (ኮምኒኬሽን) በስነ ጽሁፍ፣በቋንቋ፣ ፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና  በተዛማጅ የትምህርት መስክ፡፡ ·  የመጀመሪያ ዲግሪ 0 ዓመት የስራ ልምድ ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ የኦሮሚኛ ቋንቋ መስማት፣መናገር፣ ማንበብና መጻፍ የሚችሉ፡፡

 

ማሳሰቢያ፡

  • የምዝገባ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን  ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
  • አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • አመልካቾች በእምነት ማጉደል በማጭበርበር ወይም በስርቆት ወንጀል ተከሰዉ ከሆነ ስልጣን ባለዉ አካል ተፈርዶባቸዉ የመቀጠር መብታቸዉን እንዲጠቀሙ ስልጣን ያለዉ ፍርድ ቤት የወሰነበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ኦርጅናሉን የትምህርት መረጃ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ከተጠቀሰዉ የትምህርት ዝግጅት ውጭ ለምዝገባ የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተቀባይነት አይኖራቸዉም፡፡
  • አመልካቾች መልካም ስነ-ምግባር ያለው/ላት፣ ከማንኛውም ደባል ሱስ የፀዳ/ች፣ጥሩ ስብዕና ያላቸው መሆን አለባቸው ፡፡
  • ተወዳዳሪዎች በተመዘገቡበት የስራ መደብ ለምን ተቀጥረው መስራት እንደፈለጉ በጽሁፍ ገልፀው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • አመልካቾች የሙያ ብቃት በሚያስፈልጋቸው የት/ት ዝግጅት የብቃት ማረጋገጫ በማስታወቂያው በተጠየቀው የት/ት ደረጃ ልክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የሙያ ብቃት ምዘና ያልተጀመረባቸው የትምህርት መስኮች ከሚመለከተው ተቋም የሙያ ብቃት አለመጀመሩን ማስረጃ ካቀረቡ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
  • የኮንትራት ቅጥሩ ለ6 ወር ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ በየ6 ወሩ ይታደሳል፡፡
  • ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ በሌላ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
  • አመልካቾች የምትመዘገቡበት ሊንክ በዌብሳይታችን ameco.et ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
  • ወይም በተከታዩ ሊንክ https://forms.gle/97LaYYnMuRmQCyJz8  በመጫን መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እናሳስባለን፣
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 226 5007 አሚኮ ባህር ዳር ይደዉሉ፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባሕር ዳር

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here