0
24

ፓርኩ በደቡብ ክልል በጋሞ ጐፋ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ አቅራቢያ ነው የሚገኘው:: ከአዲስ አበባ 500፤ ከአዋሳ ደግሞ 275 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው የተከለለው:: የፓርኩ ስፋት 514 ኪሎ ሜትር ስኩዌር ተለክቷል::

ፓርኩ  በ1974 ዓ.ም ነው የተመሰረተው። በ1991 እ.አ.አ በዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃም ድርጅት ድንበሮቹ ተለይተው እውቅና አግኝቷል::

የፓርኩ መገኛ መለካምድራዊ አቀማመጥ ዝቅተኛው ጫሞ ሀይቅ ከመሬት ወለል በላይ 1,108 ሜትር፣ ከፍተኛው የታባላ ተራራ 1,650 ሜትር ተለክቷል:: በቀጣናው ዝናብ የሚጥልባቸው ወራት ከመጋቢት እስከ ግንቦት ሲሆን ዓመታዊ አማካዩም 900 ሚሊ ሜትር ነው::

በዓየር ንብረቱ ቀዝቃዛው 28 ሞቃቱ ደግሞ 35 ዲግሪ ሴልሺየስ መሆኑን ድረ ገፆች አስነብበዋል:: ከፓርኩ ስፋት 15 በመቶ  በአባያ እና ጫሞ ኃይቆች እንዲሁም የሰርማሌ እና ቁልፎ ወንዞች ውሃ የተሸፈነ ነው ::

የፓርኩ ሜዳማ ቀጣናዎች በሳር፣ ኮረብታዎች እና ተዳፋታማ አቀበቶች እንዲሁም በቁጥጧጦ የተሸፈኑ ናቸው:: በፓርኩ ከዱር እንስሳት የሜዳ አህያ፣ ተኩላ “ዲክዲክ፣ አኑቢስ ባቡን፣ ስዋይን ኽርት ቢስት እና ቀበሮ መኖራቸው ተረጋግጧል::

ከአእዋፍ 333 ዝርያዎች ከነዚህ ውስጥ ሦስቱ በሌላ ቦታ የማይገኙ ብርቅዬ መሆናቸውንም ድረ ገፆች አመላክተዋል::

ወደ ፓርኩ ለመድረስ ከአዲስ አባ በተሽከርካሪ አሊያም በአውሮኘላን አርባ ምንጭ ደርሶ መጐብኘት ይቻላል::

ዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ቪዚት ኢትዮጵያ፣ ናሽናል ፓርክ ወርልድ ዋይድ እና ወርቅ አምባቱርን ተጠቅመናል::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሚያዚያ 5  ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ

በhttp:// www.ameco.et/Bekur

በቴሌግራም – https://t.me/bekur123 ላይ ማግኘት ይችላሉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here