በምሥራቅ ጎጃም ዞን የብቸና ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁም መሰረት ሎት 01. የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ ሎት 02. የህንጻ መሳሪያ እቃዎች እና ሎት 03. የኮፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች ሲሆኑ መጫረት ለሚፈልጉ የጨረታ መመሪያው እንደሚከተለው ነው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች ላይ መጫረት የሚችሉት የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ ሲሆኑ በሌሎች ሎቶች ላይ ደግሞ የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ መጫረት የሚችሉት የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ ናቸዉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ መሻጫ ዋጋ ለእያንዳንዱ ሎቶች ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከብቸና/ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን የሚያስተጓጉል ሂደት ከሌለ በስተቀር ጨረታው ይከፈታል፡፡ አሸናፊ የሆነው ተጫራችም በጨረታው ይገደዳል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ፖስታቸዉን በማሸግ ከፖስታውና ከጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱን ማህተም እና ፊርማ ተቀምጦ በኮሌጃችን ግ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በሚገኘዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ሰዓቱን ጠብቆ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የተወዳደሩበትን ዋጋ አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ ገንዘቡን ለገ/ያዥ ገቢ አድርገው የተከፈለበትን ደረሰኝ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል ይዞ ንብረቱን ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- ተጫራቾች ንብረቱን በራሳቸው ወጭና ትራንስፖርት ኮሌጁ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ኮሌጁ በሚቀርቡለት እቃዎች ላይ እስከ 20 በመቶ መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የሚታየዉ በሎት ነዉ፡፡ ሥርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 665 14 98 /058 665 13 68 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የብቸና ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ለኮሌጁ

