የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
12

በአፈ/ከሳሽ ካሳሁን አዳሙ እና በአፈ/ተከሳሽ እነ አብየ ቢተው 2ቱ ራሳቸው መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በቲሊሊ ከተማ 02 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ ወንዴ ገ/መደህን፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን መለሰ የኔነህ እንዲሁም በደቡብ መዳኒት በሬ እንዲሁም በሰሜን ስመኝ ጌታቸው የሚያዋስነውን መኖሪያ ቤት በእነ አብየ ቢተው ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,210,611.47 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ አስር ሺህ ስድስት መቶ አስራ አንድ ብር ከአርባ ሰባት ሳንቲም) ስለሚሸጥ  ማስታወቂያን ለ30 ተከታታይ ቀናት ማለትም ከሚያዚያ 5/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 04/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ በማዋል ግንቦት 05/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡30 እስከ 6፡00 እንዲሸጥ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 ኛውን በሲፒኦ ይዛችሁ እንድትቀርቡ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here