ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
24

የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት 1. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ 2. የመኪና ጎማ ፣3. የመኪና መለዋወጫ እና 4. የብስክሌት ጎማ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ ከመንግስት የሚጠበቅባቸዉን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የግዥዉ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ለጨረታው የተዘጋጀውን ሠነድ ቢሮ ቁጥር 09 በአካል በመቅረብ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታው ሠነድ ያለምንም ስርዝ ድልዝ መሞላት ይኖርበታል፡፡
  4. የተሞላው ዋጋ ቫትን የሚጨምር ወይም የማይጨምር መሆኑ መገለጽ ይኖርበታል፡፡ የተገለጸ ነገር ከሌለው ከቫት ጋር እንደተሞላ ይቆጠራል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዛቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ከሠነዱ ጋር አብሮ አያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  6. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡
  7. የጨረታው ዝርዝር ጉዳይ በጨረታ መመሪያው ላይ ይገኛል፡፡
  8. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በአካል ቢሮ ቁጥር 013 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 2719/058 220 5269 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here