አንጋፋዉ ርግብ

0
17

በአሜሪካ የሚዙሪ ከተማ ኗሪው የ77 ዓመቱ ዲዋይን ኦሬንደር ያሳደጉት 44 ዓመታትን ያስቆጠረ ርግብ በዓለም አቀፉ የድንቃ ድንቅ መዝጋቢ ድርጀት “ህያው እድሜ ጠገብ ርግብ” በሚል ስያሜ ለክብረ ወሰን መብቃቱን ዩፒአይ ድረ ገጽ ለንባብ አብቅቶታል::

የዓለም አቀፉ ድንቃ ድንቅ መዝጋቢ ተቋም በመረጃ ምንጭነት እንዳሰፈረው የ77 ዓመቱ ኗሪ “ሱገር” ሲሉ የሚጠሩት ርግብ ቀደም ብሎ  “ማቱሳላ” በሚል ከሚጠራው በጀርመኑ  “ማቱሳላ” በተሰኘው ርግብ ከተያዘው ክብረ ወሰን በ15 ዓመታት የበለጠ ነው::

ርግቦች በአማካይ የ20 ዓመታት እድሜ  ያላቸው መሆኑን ያስነበበው ድረ ገጹ የ44 ዓመታት እድሜ ጠገቡ  ርግብ ግን በአዛውንቱ አሳዳሪው የተለየ እንክብካቤ የተደረገለት ለመሆኑ እድሜው አመላክች መሆኑ ነው የተጠቆመው::

አዛውንቱ እድሜ ጠገቡ ርግብ ከተፈለፈለበት እለት ጀምሮ በመኖሪያ ቤታቸው መኖሩን ነው የገለጹት:: ርግቡ “ሮዝ” የተሰኘች ጓደኛ እንደነበረችው እና ከ30 ዓመታት በፊት (በ1996 እ.አ.አ) መሞቷን አስረድተዋል::

በአንድ ጣሪያ ስር ሲኖሩ ከአዛውንቱ ጋር በረፍት ጊዜያቸው ጭናቸው ላይ ቁጭ ብሎ ቴሌቪዥን መመልከት እና ሙዚቃ ማዳመጥ እንደሚወድም ተናግረዋል::

በመጨረሻም  ላለፉት 50 ዓመታት በሙዚቃ ስራ ላይ መሰማራታቸውን የገለጹት አዛውንቱ ርግቡ በተለያዩ የሙዚቃ “ክሊፖች” ቀረፃ ላይ መካተቱን ስለማውሳታቸው ድረ ገጹ አስነብቧል::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሚያዚያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here