አንጐል ሌላው የውፍረት መቀነሻ

0
12

በአሜሪካ የኦክላሃማ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በተፈጠሯዊ “ኤፍጂኤፍ21” የተሰኘ ሆርሞን ላይ አነጣጥረው የምግብ መፈጨትን እና ፍላጐትን ለመቆጣጠር የሚረዱ መልእክቶችን ወደ አንጐል በመላክ ከመጠን ያለፈ ውፍረትን መቀነስ እንደሚቻል መገንዘባቸውን ሳይንስ ዴይሊ  ድረ ገጽ አስነብቧል::

ተመራማሪዎቹ “ኤፍ ጂ ኤፍ 21” ወይም (ፋይብሮ ብላስት ግሮውዝ ፋክተር 21) በመባል የሚታወቀው ሆርሞን (እድገተ ንጥር) የምግብ ፍላጐትን ለመቆጣጠር የሚረዱ ምልክቶችን ወደ አንጐል በመላክ እንደሚሰራ ደርሰውበታል::

የተጠቀሰው ሆርሞን በአንጐል የኃለኛው ክፍል እንደሚገኝ እና እንደሚሰራ ነው የለዩቶ – ተመራማሪዎቹ::

ዋና ተመራማሪው ዶክተር ማቲው ፓት”ሀፉ እንደገለጹት የምርምር ቡድኑ በአንጐል የኋለኛው ክፍል ሆርሞኑ የሚያስከትለውን ለውጥ መረዳት ላይ አትኩረው ሰርተዋል::

በምርምሩ ውጤትም የአንጐል የኋለኛው ክፍል ከሌሎች ክፍሎች ጋር በመገናኘት ምግብ ወደሚፈጭበት ምልክት በማስተላለፍ ተፅእኖ ለማሳደር እና ክብደትን መቀነስ እንደሚቻል ነው የተገነዘቡት::

ዋና ተመራማሪው ማቲው ፖትሆፍ “ኤፍጂ ኤፍ 21” ሆርሞን በማነሳሳት ከመጠን ያለፈ ውፍረትን ወይም “ኦቤሲቲ” ለመቀነስ ወይም ለማስተካከል የጐንዮሽ ጉዳቶች ሳይኖሩ ውጤታማ የህክምና ተግባራትን መከወን እንደሚቻል ባለሙሉ ተስፋ መሆናቸውን ነው ያሰመሩበት::

ዋና ተመራማሪው ቀደም ብሎ በምርምር የተገኙ “ዲ ኤልፒ-1” የተሰኙ መድሃኒቶች የምግብ ፍላጐትን እና የምግብ ቅበላን እንደሚቀንሱ ጠቅሰው “ኤፍጂ ኤፍ 21” ግን የምግብ መፈጨትን በመጨመር የበለጠ ኃይል እንዲቃጠል እና በድምሩ ክብደትን ለመቀነስ እንደሚረዳ በመግለፅ ነው ያደማደሙት::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሚያዚያ 19  ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here