ክብረወሰን ያስመዘገበው

0
12

በቻይና አንሁይ ግዛት ኢሃንግ ኤግሬት የተሰኘው ኩባንያ በ22580 ድሮኖች ህብር ፈጥሮ ለእይታ ባበቃው አስደናቂ ብርሃን ፈንጣቂ ቅርጽ አዲስ የዓለም ክብረወሰን ማስመዝገቡን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ሰሞኑን አስንብቧል:: ባለፉት ጥቂት ዓመታት በቻይና የሚገኙ ኩባንያዎች በሌሊት አስደናቂ ቅርፅ ያላቸው የብርሃን ትሪኢቶችን አዘጋጅተው ለእይታ በማብቃት የዓለም ክብረወሰንን ሲሰብሩ ተስተውሏል::

በዚህ ዓመት የካቲት ወር በጓንግዶንግ የሚገኝ ኩባንያ በ22580 በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚሰሩ ብርሃን ፈንጣቂ ድሮኖች ህብር ፈጥሮ በባለ ሦስት ማእዘን ቅርፅ ለእይታ ባበቃው የቻይና ባህላዊ ፋኖስ ቅርጽ አዲስ ክብረወሰን አስመዝግቧል:: በዚህም ሀገሪቱ ከሌሎች በበለጠ በቴክኖሎጂው መምጠቋን ያሳያችበት ነው ተብሏል:: ትርኢቱ በድሮኖች ህብር ልዩ ምስል ከመስራት ባለፈ ለጦርነትም ድሮኖችን መገልገል ስለሚቻል በጦር ኃይል የበላይነትን ለማሳየት በማለም ለእይታ ማብቃቷ ነው በድረ ገጹ የተጠቆመው::

ብርሃን ፈንጣቂ ድሮኖቹ በመንጋ በመትመም በዓየር ላይ እንዲሰሩ እና እንዲያሳዩ የተፈለገውን ቅርጽ በሚፈለገው መልኩ ማሳየት መቻላቸውም ተገልጿል:: ይህም ሀገሪቱ በያዝነው ዘመን የጦር ኃይል አቅሟን ማሳየትን አልማ በቴክኖሎጂው በዓለም አቀፍ ደረጃ  ቀዳሚነቷን ለማመላከት ያዘጋጀችው ሊሆን እንዲመችል ነው ወታደራዊ ባለሙያዎች አስተያየታቸውን በመስጠት ያሰመሩበት::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here