የኬንያ ተራራ ብሔራዊ ፓርክ

0
12

በኬንያ ማእከላዊ ክልል ውስጥ በከፍታው ከኪሊ ማንጃሮ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ተራራ  ነው ማውንት ኬንያ::ከፍተኛው ጫፍ 51 99 ሜትር ተለክቷል::

የፓርኩ ቀጣና ከዋና ከተማዋ ናይሮቢ 193 ኪሎ ሜትር ወይም ሀገሪቱን  ከሚያዋስናት ድንበር ወደ ውስጥ 480 ኪሎ ሜትር ገባ ያለ ነው:: የፓርኩ አጠቃላይ ስፋት 2800 ስኩዌር ኪሎ ሜተር ተለክቷል::

ፓርኩ  በ1968 እ.አ.አ በብሔራዊ ፓርክነት የተመሰረተ ሲሆን ከዚያ ቀደም ባሉት ዓመታት ግን በደን ቀጣናነቱ ነበር የሚታወቀው:: በ1978 እ.አ.አ በዓለም አቀፉ የአካባቢ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት “የባዮስፌር ሪዘርቭ” ተብሎ ተሰይሟል::በ1997 እ.አ.አ ያለውን አስደናቂ ገፅታ እና የደን ክምችት ለመጠበቅ በዓለም ቅርስነት መመዝገቡንም ድረ ገፆች አስነብበዋል::

በመልካም ድራዊ አቀማመጡ በደን የተሸፈነ ተራራ፣ የሳር ምድር እና ከፊል ደረቅ የሳር ምዳር ስነምህዳርን አቅፎ ይዟል::

በፓርኩ ከዱር አራዊት ዝሆን፣ ጥቁር አውራሪስ፣ ጦጣ፣ ዠንጉር ጉር ጅብ፣ ዝንጀሮ እና የሜዳ አህያ መገኘታቸው ተረጋግጧል::

ከዓእዋፍ 130 ዝርያዎች  መገኘታቸውን ድረ ገፆች አስነብበዋል:: በቀጣናው የሚገኙ ተራራዎች አናት ቀደም ባሉት ምእተ ዓመታት በበረዶ የተሸፈኑ ነበሩ- አሁን ላይ ግን በዓየር ንብረት ለውጥ መጥፋታቸው ነው የተጠቆመው:: በስም ከተጠቀሱት ተራራዎች ሊናና 4985 ሜትር፣ኒሊዮን 5188፣ ባቲያን 5199 ሜትር ከፍታ ያላቸው መሆኑም በማጠቃለያነት ለንባብ በቅቷል::

ለፓርኩ ብዝሃ ህይወት መጠበቅ እና ዘላቂነት የደን መጨፍጨፍ፣ ልቅ ግጦሽ፣ አደን እና የሰደደ እሳት ስጋት መሆናቸውም ነው የተጠቆመው::

ለዘገባችን ኬንያ ሳፋሪ፣ ሚት ኬንያ ፓርክ፣ ሚት ኬንያን ሳፋሪ ቱር እና ዩኔስኮ- ድረ ገፆችን በመረጃ ምንጭነት ተጠቅመናል::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here