ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
13

የደብረ ታቦር  ከተማ  አስተዳደር ከተማ  መሰረተ ልማት  መምሪያ  በ2018 በጀት  ዓመት  ለመግዛት ካቀደቸው የኤሌክትሮኒክስ  እቃዎች  እና የጽህፈት መሳርያ ግዥዎች ውስጥ 1ኛ.   ዲሰክቶፕ ኮምፕዩተር በቁጥር 02፣ ላፕቶፕ በቁጥር 01፣ ፍለሽ  በቁጥር 15፣ 2ኛ. ፕሪንተር ኢንክ  በቁጥር 40  ሆኖ 26 A ብዛት 5፣ 80 A ብዛት 22፡ 59A ብዛት 13፣ የፕሪንተር ወረቀት A4/80 ግራም/ በደስታ 200፣ ሰማያዊ  ቢክ እስክብሪቶ /ኦርጅናል ሰማሳዊ /በባኮ 20 በግልጽ  ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶችን  የሚያሟሉ  ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ  የንግድ  ፈቃድ  ያላቸው፡፡
  2. ያቀረቡት ዋጋ  ከብር 200,000 (ሁለት መቶ  ሽህ  ብር) እና  በላይ  ከሆነ  የቫት  ተመዝጋቢ መሆኑን  የሚገልጽ  ማስረጃ  ማቅረብ  የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ከተራ  ቁጥር 1-2  የተዘረዘሩትን  መረጃዎች  ከዋናው  ጋር  የተገናዘበ  ፎቶ  ኮፒ  ከጨረታ  ሰነዶቻቸው  ጋር  አያይዘው  ማቅረብ  አለባቸው፡፡
  4. ለተራ ቁጥር 1 የኤሌክትሮኒክ እቃዎች እና ለተራ ቁጥር 2 የጽህፈት መሳሪያ  የንግድ  ፈቃድ   ያላቸው፡፡
  5. የግዥው ዝርዝር  መግለጫ (ስፔስፊኬሽን)  ከጨረታ  ሰነድ  ማግኘት  የሚቻል  ሲሆን  የሰነድ  መግዣ  ዋጋ  ብር  300  (ሶስት መቶ ብር) ነው፡፡
  6. በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ  ይሆናል፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ  ማስከበሪያ  የሚወዳደሩበትን  የእቃውን  ጠቅላላ ዋጋ ለተራ ቁጥር 1  ብር 6,000 (ስድስት ሽህ  ብር) ለተራ ቁጥር 2,  ብር 5000 (አምስት ሽህ ብር) በተረጋገጠ  የክፍያ  ትእዛዝ  (ሲፒኦ) ወይም  በጥሬ  ገንዝበን ማሳያዝ አለባቸው፡፡
  8. ጨረታ ሳጥን በግዥ ፋይናስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ይገኛል፡፡
  9. የጨረታ ሰነድን ቢሮ ቁጥር 14 ይገኛል፡፡
  10. ጨረታው ከወጣበት ቀን  ጀምሮ  ባሉት 15   ተከታታይ  ቀናት  ይቆያል፡፡  ውድድሩ  በእያንዳንዱ  ሎት  ድምር  መሆኑን  እንገልጻለን፡፡  የእያንዳንዱን  ሎት  ሁሉንም  ዝርዝር  ያልሞላ  ከውድድር  ውጭ  ይሆናል፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ የሞላበትን ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለበት፡፡
  12. ጨረታው በ16ኛው  ቀን  በ4፡00 ታሽታ  በዚያው  ቀን  4፡30  ተጫራቾችና  ህጋዊ  ወኪሎቻቸው  በተገኙበት  ይከፈታል፡፡ ነገር  ግን  የመጨረሻው  ቀን  በዓል  ከሆነ  በሚቀጥለው  የስራ  ቀን  በ4፡00 ታሽጎ  4፡30  ይከፈታል፡፡
  13. 2014 ዓ/ም የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ያወጣውን አዲስ የተሻሻለ የግዥ መመሪያ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ  ጨረታውን  ሙሉ  በመሉ  ወይም  በከፊል  የመሰረዝ  መብቱ  የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 00 58 /058 141 00 91 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደብረታቦር  ከተማ  አስተዳደር  ከተማ  መሰረተ ልማት  መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here