በአፈፃፀም ከሳሽ አብሮ ማደግ እቁብ ማህበር እና በተከሳሽ ይርጋ ፍቃዱ መካከል ባለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ ተከሳሽ የተወሰነበትን እዳ ለመክፈል ፍቃደኛ ባለመሆናቸው በፍርድ ባለዳ አቶ ማተቤ አሸንፍ ስም በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ ፣ በምዕራብ ልቅና ክንዴ፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ ክንዴ ሰውነት መካከል የሚገኘው መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,468,559 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ስልሳ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ሃምሣ ዘጠኝ ብር) በማድረግ ከሚያዝያ 26/2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ግንቦት 27/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡00 እስከ 5፡00 የጨረታው ንብረት ባለበት ቦታ የሚከናወን በመሆኑ ተጫራቾች የንብረቱን ግምት 1/4 በሲፒኦ አስይዘው በመቅረብ መወዳደር ወይም መግዛት የሚችሉ መሆኑን አውቃችሁ ውጤቱን ከቀኑ 7፡00 ይዛችሁ እንድትቀርቡ ሲል ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡
የጓጉሳ ሽጉዳድ ወረዳ ፍርድ ቤት

