ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
8

በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ”EU በጀት ሎት 1. ጋቢዮንና የጋቢዮን ማሰሪያ ሽቦ በመደበኛ በጀት ለተሁለደሬ እንስሳት ሀ/ል/ጽ/ቤት፣ ሎት 2. የእንስሳት መድሃኒት እንዲሁም ሎት 3. የእንስሳት ህክምና መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  4. ጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት ለተቀመጡ ግዥዎች ብር ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር)፣ ሎት 2 እና 3 ለተቀመጡ ግዥዎች ለእያንዳንዳቸው ብር 20,000 (ሀያ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ተሁለደሬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ግንቦት 03/2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታዉ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ (ባይገኙም ይከፈታል) የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የመክፈቻ ሰዓቱን ጠብቆ ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊው የሚለየው በሎት (በድምር) ዋጋ ነዉ፡፡ በሰነዱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታዉ ዉጭ ይሆናል፡፡ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠዉ ተጫራች መ/ቤቱ በጠየቀዉ (ስፔስፊኬሽን) መሰረት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  9. ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር የተጋነነ ከሆነ ጨረታዉ ዉድቅ ይሆናል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ (በከፊል) የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ሁሉም የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸዉን የጠበቁ መሆን አለባቸዉ፡፡ አሸናፊው ድርጅት እቃዎቹን ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ወጭ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን ከየንብረት ክፍሉ አስረክቦ ገንዘቡን ወጭ አድርጎ ይወስዳል፡፡
  12. ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብና ዋጋ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታዉ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
  13. ጨረታዉን ለማዛባት የሞከረ ተጫራች ከጨረታዉ ዉጭ ሆኖ ወደፊትም በጨረታዎች እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 00 12 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here