የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
23

የአምበር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ከዚህ ቀደም በልዩ መመሪያ ለማደያ አገልግሎት ተላልፎ የነበረ መሬት ወደ ልማት ባለመግባቱ ከባለሀብቱ በመንጠቅ ወደ መሬት ባንክ ያስገባውን መሬትና በቦታው ላይ ያረፈውን ንብረት በሊዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 እና በአፈፃጸም መመሪያ ቁጥር 1/2005 መሰረት በጨረታ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከታች በዝርዝር በተገለፀው መስፈርት መሰረት በዘርፉ መሰማራት የምትፈልጉ ሁሉ  መጫረት ትችላላችሁ ፡፡

  1. የጨረታ ቁጥር አም/ልዩ/2018 ዓ/ም ፣ የአጫራቹ መ/ቤት ስም አምበር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት፣ አድራሻ በአማራ ክልል በምሥ/ጎጃም ዞን በአነደድ ወረዳ በአምበር 01 ቀበሌ ነው፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ አምበር መሪ ማዘጋጃ ቤት ሲሆን የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 10፡00 ነው፡፡
  3. የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚፈልጉ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 10፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  5. ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ግንቦት 11/2018 ዓ.ም እና ግንቦት 12/2018 ዓ.ም በሥራ ሰዓት በተያዘው ፕሮግራም መሰረት የምናስጎበኝ መሆኑንና ከተቀመጠው ጊዜ ውጭ ለሚመጡ ተጫራቾች በግልጽ ሊያሳይ የሚችል ስዕላዊ መግለጫ እንሰጣለን፡፡
  6. ጨረታው በይፋ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ከተመሰከረለት ባንክ ህጋዊ ደረሰኝ የመነሻ ዋጋውን 20 በመቶ የገንዘብ መጠን ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች (ሲፒኦ) የሚመለስበት ጊዜ የጨረታው አሸናፊ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ይሆናል፡፡
  9. መሪ ማዘጋጃ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 058 261 00 12 በመደወል ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 04 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአምበር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here