ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
28

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በ2018 በጀት አመት የተለያዩ መኪኖች ጎማ  በግልጽ ጨረታ እቃዎች አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንየገለጽን፡-

  • በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  • የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅርብ የሚችሉ፣
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣
  • የግዥው መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  • ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በግልፅ የሚታይ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  • የግዥው መጠን ከ20,00.00 /ሀያ ሺ ብር/ በላይ ከሆነ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ ላይ 50 በመቶ የሚቆረጥባቸው መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡
  • የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከግዥ ፋይ/ንብ/አስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 17 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • የጨረታ ሰነድ የመሸጫ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ በግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 14 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 15ኛዉ ቀን 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛዉ ቀን በ3፡00 ታሽጐ 3፡30 ይከፈታል፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 320 58 38 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0981799008 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ ባህር ዳር ቀበሌ 13 ከእስፖርት ኮሚሽን ጀርባ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here