በአፈ/ከሳሽ ወ/ሮ ሙሉዓለም ተሻለ እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ ጌትነት ዳኛው መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በአገው ግምጃ ቤት ከተማ 02 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ ግብርና ጽ/ቤት፣ በምዕራብ ውዴ ቢያብ፣ በሰሜን ቴሌኮሚኒኬሽን እንዲሁም በደቡብ መንገድ የሚያዋስነው በአፈ/ተከሳሽ በአቶ ጌትነት ዳኛው ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የድርጅት /መኖሪያ ቤት/ የሆነው በመነሻ ዋጋ ብር 4,410,733.84 (አራት ሚሊዮን አራት መቶ አስር ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ ሶስት ብር ከሰማኒያ አራት ሳንቲም) ስለሚሸጥ ጨረታው ከግንቦት 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 16/2018 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ 30 ቀናት ቆይቶ ሰኔ 17/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 እንዲሸጥ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን በሲፒኦ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

