በድጋሚ የወጣ የቋሚ ቅጥር ማስታወቂያ

0
10

ቁጥር የሠ/ቅ.ማ/3150/2018

ቀን 13/09/2018 ዓ/ም

 

 

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች ያሉትን ክፍት የስራ መደቦች ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን ከሚያሟሉ ስራ ፈላጊዎች መካከል በቋሚ ቅጥር  አወዳድሮ በመቅጠርና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

 

ተቁ የሥራ መደቡ መጠሪያ ደረጃ የመ/መ/ቁ ደመወዝ ብዛት ዳይሬክቶሬት/ዝግጅት የሥራ ቦታ ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት ተፈላጊ የስራ ልምድ
1  

የአረብኛ ቋንቋ ከፍተኛ ሪፖርተር 2

12 አሚ-1525

 

በኮርፖሬሽኑ የደመወዝ ስኬል መሠረት 01 አዲስ አበባ ኅብር ዝግጅት አዲስ አበባ በብሮድካስት ጋዜጠኝነት፣ በጋዜጠኝነትና ተግባቦት፣ በተግባቦት (ኮሙኒኬሽን)፣ በስነ-ጽሁፍ፣በቋንቋ፣ ፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና  በተዛማጅ የትምህርት መስክ  የሰለጠነ ·  የመጀመሪያ ዲግሪና  3 ዓመት   ወይም ሁለተኛ ዲግሪ

1 ዓመት አግባብንት ያለው/ት የስራ ልምድ

·       ከአማርኛ ቋንቋ  በተጨማሪ የአረብኛ ቋንቋ መስማት፣ መናገር፣ ማንበብና መጻፍ የሚችል/የምትችል

2 የአፋርኛ ቋንቋ ከፍተኛ ሪፖርተር 2 12 አሚ-1500

 

በኮርፖሬሽኑ የደመወዝ ስኬል መሠረት 01 አዲስ አበባ ኅብር ዝግጅት አዲስ አበባ በብሮድካስት ጋዜጠኝነት፣ በጋዜጠኝነትና ተግባቦት፣ በተግባቦት (ኮሙኒኬሽን)፣በስነ-ጽሁፍ፣ በቋንቋ፣ ፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና  በተዛማጅ የትምህርት መስክ የሰለጠነ ·  የመጀመሪያ ዲግሪና  3 ዓመት  ወይም ሁለተኛ ዲግሪ

1 ዓመት አግባብነት ያለው/ት የስራ ልምድ

·       ከአማርኛ ቋንቋ  በተጨማሪ የአፋርኛ ቋንቋ መስማት፣ መናገር፣ ማንበብና መጻፍ የሚችል/የምትችል

 

ማሳሰቢያ፡-

  • የምዝገባ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን  ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
  • አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ፣ የትምህርት ማስረጃቸውን ኦርጅናል ከማይመለስ ኮፒ ጋር ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • አመልካቾች በእምነት ማጉደል ፣በማጭበርበር ወይም በስርቆት ወንጀል ተከሰዉ ስልጣን ባለዉ አካል ተፈርዶባቸዉ የመቀጠር መብታቸዉን እንዲጠቀሙ ስልጣን ያለዉ ፍርድ ቤት የወሰነበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ከተጠቀሰዉ አግባብነት ያለው የትምህርት ዝግጅት ውጭ ለምዝገባ የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተቀባይነት አይኖራቸዉም፡፡
  • አመልካቾች መልካም ስነ-ምግባር ያላቸው፣ ከማንኛውም ደባል ሱስ የፀዱ፣ጥሩ ስብዕና ያላቸው፡፡
  • ተወዳዳሪዎች በተመዘገቡበት የስራ መደብ ለምን ተቀጥረው መስራት እንደፈለጉ በጽሁፍ ገልፀው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • አመልካቾች የሙያ ብቃት በሚያስፈልጋቸው የትምህርት ዝግጅት የብቃት ማረጋገጫ በማስታወቂያው በተጠየቀው የትምህርት ደረጃ ልክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የሙያ ብቃት ምዘና ያልተጀመረባቸው የትምህርት መስኮች ከሚመለከተው ተቋም የሙያ ብቃት አለመጀመሩን ማስረጃ ካቀረቡ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
  • በግል የተሰራባቸው የስራ ልምደች የስራ ግብር የተከፈለበት ማስረጃ ከገቢዋች ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ከአንድ የስራ መደብ በላይ መመዝገብ አይቻልም፡፡
  • የፈተና ቦታና ፈተና የሚሰጥበት ቀን በሌላ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
  • አመልካቾች የምትመዘገቡበት ሊንክ በዌብሳይታ ameco.et ማግኘት ትችላላችሁ ወይም ይህ ሊንክ በመጫን ይመዝገቡ https://forms.gle/ijtUjSyLbEokqr1y8  መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here