የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
6

በፍ/ባለመብት አቤልነህ እጅጉ ህንፃ ላይ የሚጣል እቁብ  እና በፍርድ ባለ እዳ አቶ ባድማው ታረቀኝ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በቁጭ ከተማ ቀበሌ 02 ክልል ውስጥ የሚገኘውን የፍርድ ባለ እዳ ንብረት የሆነውን በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ባድማው፣ በሰሜን ሙላቱ ዲንቃ እንዲሁም በደቡብ መላኩ ቢዘንጋው የሚያዋስነው 400 ካ.ሜ የመኖሪያ ቤት የግምቱ መነሻ ዋጋ ብር 1,226,996 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃያ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስድስት ብር)በጫረታ ይሸጣል፡፡ ጨረታው የሚካሄድበት ቀን ሐምሌ 01/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ የባለእዳው ንብረት በጨረታ መግዛት የምትፈልጉ ሁሉ ከላይ በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን አሸናፊው እንደታወቀ የሽያጭ ገንዘብ ውስጥ ቢቻል ሙሉውን ካልተቻለ ¼ ኛውን በምዕራብ ጎጃም ዞን ከ/ፍ/ቤት በሞዴል 85 የሚያስይዙ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- በአዋሳኝ የተጠቀሰው ቤት 400 ካ.ሜ ቦታ ላይ የተሰራ ቤት በ301.28 ካ.ሜ ቦታው ላይ ባረፈበት ዳሽን ባንክ ለብር 900,000 (ዘጠኝ መቶ ሺህ ብር) ብድር የመያዣ ያለው ነው፡፡

የምዕራብ ጎጃም ዞን ከ/ፍ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here