ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
12

ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩ ደንበኞች ከባንኩ የተበደሩትን ገንዘብ መመለስ ስላልቻሉ ለብድሩ አመላለስ በመያዣ ያስያዟቸውን ንብረቶች ባንኩ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ 1ኛ. አቶ እሱባለው ተፈራ ዋስትና ሰጭ የቤቱ ባለቤት አቶ ብርሃኑ ተፈራ ወርቄ አድራሻ በፍኖተ ሰላም ከተማ፣ ቀበሌ 02፣ ካርታ ቁጥር 9-111-11-2015 የሆነ፣ የቦታው ስፋት 212.5 ካ.ሜ የሆነ በአዋሳኝ በሰሜንና በምሥራቅ መንገድ፣ በደቡብ ይህዓለም መኮንን እንዲሁም በምዕራብ ደመላሽ መኮንን የሚያዋስነውን የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ግምቱ ብር 5,637,467.37 (አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ሰባት ብር ከሰላሳ ሰባት ሳንቲም) በጫረታ ይሸጣል፡፡ 2ኛ. አቶ ንጉሴ አለም ምስክር በራሱ ስም የተመዘገበ የመኖሪያ ቤት አድራሻ በፍኖተ ሰላም ከተማ፣ ቀበሌ 02፣ በካርታ ቁጥር 471/2/2015፣ የቦታው ስፋት 200 ካ.ሜ የሆነ  በሰሜን ሀሚድ ሁሴን፣ በደቡብ አለባቸው አያሌው፣ በምሥራቅ መንገድ፤  እንዲሁም  በምዕራብ ኡመር አሊ የሚያዋስነው የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 4,494,466 (አራት ሚሊዮን አራት መቶ ዘጠና አራት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ስድስት ብር) ሆኖ ይሸጧል፡፡ ስለሆነም የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎች እና ደንቦች የሚያሟሉ  ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ጨረታው ሃምሌ 01/2018 ዓ.ም በፍኖተ ሰላም ከተማ ከዋናው አደባባይ ከፍ ብሎ ካለው ፀደይ ባንክ ፍኖተ ሰላም ቅርንጫፍ ከረፋዱ 3፡00 እስከ 6፡00 ይሆናል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ሲቀርቡ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ  እንዲሁም ድርጅት ከሆነ የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ፣ የተወካዩን ሰው ውክልና እና የድርጅቱን ህጋዊ ሰውነት ያገኘበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ለመንግስት የሚከፈሉ ማንኛውም ግብር ቫትን ጨምሮ ከቦታውና ቤቱ ጋራ የተያያዘ ክፍያ እንዲሁም ስም ለማዛወር የሚወጡ ወጭዎች በተጫራቾች ወይም በገዥ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊው ውጤቱን በሚመለከተው አካል ፀድቆ አሸናፊነቱ በተረጋገጠ በ15 ቀን ውስጥ ያሸነፈበትን ሙሉውን ገንዘብ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ አለበት፡፡ ገንዘቡን ገቢ ካላደረገ ያስያዘው ¼ ኛው የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው እንደገና ይወጣል፡፡
  6. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 775 11 54 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ፀደይ ባንክ ፍኖተ ሰላም ዲስትሪክት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here