የአዲስ ዘመን ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሠረት በ2018 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ጨረታ የድርጅት 8 ቦታዎችን ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው ቀን በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በከተማ መሠረተ ልማት ጽ/ቤት ግቢ ከጠዋቱ 3፡00 ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 31 73 72 ወይም 09 37 81 60 41 ደውሎ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአዲስ ዘመን ከተማ አስተዳደር መሬት አስተዳደር ጽ/ቤት

