ዘንባባ የንብ እና የተፈጥሮ ሃብት ውጤቶች ልማትና ግብይት ኀ/ስ/ማ/ዩኒየን በነበረበት የአሰራር ችግር ድጋፍ እና ክትትል ቢደረግለትም ከችግሩ ሊወጣ ባለመቻሉ፤ በጠቅላላ ጉባኤ እንዲፈርስ የተወሰነ በመሆኑ፤ የዩኒየኑ ሃብት እና ንብረት ከመከፋፈሉ በፊት የሃብት ወይም የገንዘብ ጠያቂ ካለ ማስረጃውን በመያዝ ከዩኒየኑ ጽ/ቤት እንዲወስድ ህዳር 15/2018 ዓ/ም በጋዜጣ በወጣው ማስታወቂያ ጥሪ የተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ እስካሁን ድረስ ይገባኛል የሚል አልቀረበም፤ የዩኒየኑ ሃብት እና ንብረቱን ከመከፋፈሉ በፊት የንብረት ጠያቂዎች ካሉ በዩኒየኑ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲወስዱ እንጠይቃለን፡፡ አድራሻ ባሕር ዳር ከተማ አጼ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ አሽርፍ ፋብሪካ ከዋናው አስፖልት መንገድ 500 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0937415896 ወይም 0918015747 መደወል ይቻላል፡፡
የአብክመ የኀብረት ሥራ ኮሚሽን

