የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
4

በአፈ/ከሳሽ ቲሊሊ ሔርሜላ ሆቴል የሚጣል አፍሪካ የእቁብ ማህበር እና በአፈ/ተከሣሾች እነ አሳየ አይቸው /22/ ሰዎች መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ

1ኛ. በአፈጻጸም ተከሣሽ በወ/ሮ የሺ አስረስ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው በአንጅባራ ከተማ 02 ቀበሌ በካርታ ቁጥር 467/08 በምሥራቅ የልጅማር፣ በምዕራብ ወርቅነህ ዘለቀ፣ በደቡብ አሰማረ ካሣሁን እንዲሁም በሰሜን መንገድ የሚያዋስነው በመነሻ ዋጋ ብር 3,140,000 (ሶስት ማሊዮን አንድ መቶ አርባ ሽህ ብር) በማድረግ ጨረታውን ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ በማዋል ጨረታው ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ቤቱ በሚገኝበት ቦታ ማጫረት ይፈልጋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ከተገኘም 1/4 ኛውን ወዲያውኑ በከፍ/ፍ/ቤቱ በአማራ ባንከ አካውንት ቁጥር 9900017292928 በሆነ ገቢ እንዲያደርጉ እና ቀሪውን ደግሞ በቀጠሮው ቀን ይዘው እንዲቀርቡ፣ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

2ኛ. በአቶ ሞሴ ታመነ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በእንጅባራ ከተማ 04 ቀበሌ በምሥራቅ እውነቱ ታመነ፣ በምዕራብ ደረጀ አየሁ፣ በደቡብ አለነ መንግስቱ እንዲሁም በሰሜን መንገድ የሚያዋስነውን በመነሻ ዋጋ ብር 2,850,000 (ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሀምሳ ሽህ ብር)  በጨረታ ይሸጣል፡፡  ጨረታው ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ በማዋል ጨረታው በሐምሌ 16/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ቤቱ በሚገኝበት ቦታ ማጫረት ይፈልጋል፡፡ የጨረታው  አሸናፊ ከተገኘም 1/4ኛውን ወዲያውኑ በከፍ/ፍ/ቤቱ የአማራ ባንክ አካውንት ቁጥር 9900017292928 በሆነ ገቢ  አንዲያደርጉ እና ቀሪውን ደግሞ በቀጠሮው ቀን ይዘው አንዲቀርቡ፣ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

3ኛ. ተከሣሽ በአቶ ጌታየ መኮነን ከበደ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በቲሊሊ ከተማ 02 ቀበሌ በምሥራቅ ንጉሴ ካሴ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን እማሆይ ጣቃየ እንዲሁም  በደቡብ የትዋለ አየለ የሚያዋስነውን በመነሻ ዋጋ ብር 1,482,421.82 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሰማኒያ ሁለት ሽህ አራት መቶ ሃያ አንድ ብር ከሰማኒያ ሁለት ሳንቲም) በማድረግ ማጫረት ይፈልጋል፡፡ ጨረታው ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ በማዋል  በሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ቤቱ በሚገኝበት ቦታ ይካሄዳል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ከተገኘ ¼ ኛውን ወዲያውኑ በከፍ/ፍ/ቤቱ የአማራ ባንክ አካውንት ቁጥር 9900017292928 በሆነ ገቢ እንዲያደርጉ እና ቀሪውን ደግሞ በቀጠሮው ቀን ይዞ አንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

4ኛ. በአቶ ጥላሁን ካሴ አድገህ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በቲሊሊ ከተማ 02 ቀበሌ በምሥራቅ አስፖልት መንገድ፣ በምዕራብ ጌታዩ መኮነን፣ በሰሜን አማሆይ ጣቃየ እንዲሁም በደቡብ የትዋለ አየለ የሚያዋስነው በመነሻ ዋጋ ብር 1,465,549.83 (አንድ ሚለዮን  አራት መቶ ስልሳ አምስት ሽህ አምስት መቶ አርባ ዘጠኝ ብር ከሰማኒያ ሶስት ሳንቲም) ይሸጣል፡፡ ጨረታውን ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ በማዋል ጨረታው ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ቤቱ በሚገኝበት ቦታ በማጫረት መሸጥ ይፈልጋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ከተገኘም 1/4ኛውን ወዲያውኑ በከፍ/ፍ/ቤቱ የአማራ ባንክ አካውንት ቁጥር 9900017292928 በሆነ ገቢ አንዲያደርጉ እና ቀሪውን ደግሞ በቀጠሮው ቀን ይዞ አንዲቀርብ  ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

5ኛ. በአቶ አንሙት ቦጋለ ጌቴ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በቲሊሊ ከተማ 02 ቀበሌ በምሥራቅ አስፖልት መንገድ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን አለሙ ተፈራ፣ እንዲሁም በደቡብ ክፍት የማዘጋጃ ቦታ የሚያዋስነውን በመነሻ ዋጋ ብር 1,849,124.64 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ ዘጠኝ ሽህ አንድ መቶ ሀያ አራት ብር ከስልሣ አራት ሣንቲም) ይሸጣል፡፡ ጨረታው ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ በማዋል ጨረታው በሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ቤቱ በሚገኙበት ቦታ ማጫረት ይፈልጋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ከተገኘም ¼ ኛውን በከ/ፍ/ቤቱ የአማራ ባንክ አካውንት ቁጥር 9900017292928 በሆነው ገቢ አንዲያደርጉ እና ቀሪውን ደግሞ በቀጠሮው ቀን ይዞ እንዲቀርብ ሲል ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

6ኛ. በአቶ ጌትነት አያሌው ቦጋለ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ በምሥራቅ ንጋቴ ወርቁ፣ በምዕራብ ምንታምር ላቀው፣ በሰሜን ጌታነህ መኩሪያው እንዲሁም በደቡብ መንገድ የሚያዋስነውን በመነሻ ዋጋ ብር 1,325,670.11 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሀያ አምስት ሽህ ስድስት መቶ ሰባ ብር  ከአስራ አንድ ሣንቲም) በማድረግ ጨረታው ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ በማዋል ጨረታውን ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ቤቱ በሚገኝበት ቦታ  ማጫረት ይፈልጋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ¼ ኛውን ወዲያውኑ በከፍ/ፍ/ቤቱ የአማራ ባንክ አካውንት ቁጥር 9900017292928 በሆነ ገቢ እንዲያደርግ  እና ቀሪውን ደግሞ በቀጠሮው ቀን ይዞ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

7ኛ. .በአቶ አጉማስ አየነው መንግስቱ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ   በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ደሣለው መለሰ፣ በሰሜን ሞላ አየሁ እንዲሁም በደቡብ አንዳርግ መንግስት የሚያዋስነው በመነሻ ዋጋ ብር 1,762,240.66 (አንድ ሚለዮን ሰባት መቶ ስልሳ ሁለት ሽህ ሁለት መቶ አርባ ብር ከስልሳ ስድስት ሳንቲም) ይሸጣል፡፡ ጨረታውን ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ በማዋል ጨረታው በሐምሌ 22/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ቤቶች በሚገኝበት ቦታ መጫረት ይችላሉ፡፡ የጨረታው አሸናፊ 1/4ኛውን ወዲያውኑ በከፍ/ፍ/ ቤቱ የአማራ ባንክ አካውንት ቁጥር 9900017292928 በሆነ ገቢ እንዲያደርግ እና ቀሪውን ደግሞ በቀጠሮው ቀን ይዞ አንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

8ኛ. በአቶ አወቀ አልማው አበበ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሣኝ በምሥራቅ ዝግአለ ተሰማ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ቄስ አለማየሁ ታዬ እና በደቡብ ሽፈራው አሸብር የሚያዋስነውን በመነሻ ዋጋ ብር 3,011,853.30 (ሶስት ሚሊዮን አስራ አንድ ሽህ ስምንት መቶ ሀምሳ  ሶስት ብር ከሰላሳ ሳንቲም) ይሸጣል ፡፡  ጨረታው  ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ በማዋል ጨረታው በሐምሌ 23/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ቤቱ በሚገኝበት ቦታ ማጫረት ይፈልጋል፡፡ የጨረታው አሸናፊው 1/4ኛውን ወዲያውኑ በከፍ/ፍ/ቤቱ የአማራ ባንክ  አካውንት ቁጥር 9900017292928 በሆነ ገቢ እንዲያደርግ እና ቀሪውን ደግሞ በቀጠሮው ቀን ይዞ አንዲቀርብ በማድረግ በጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ በቦታው ተገኝታችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ ያስታውቃል፡፡

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከፍ/ቤት

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here