ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
53

በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 በሚገኜው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት 1. በቆሉ ሽያጭ፣ ሎት 2. ጤፍ ሸያጭ፣ ሎት 3. ሩዝ ሽያጭ እና ሎት 4. የዱቄት ማበልጸጊያ  ማሽን ግዥ በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ካላቸው አወዳድሮ መግዛትና መሸጥ ይፈለጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ /ዋስትና/ ወይም ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅርቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ግልጽ ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበስብባቸዉ ፈቃድ የተሰጠሠቸዉ (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥዉ የሚሳተፍ ማንኛዉም ተጫራች ተጨማሪ እስት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና ሲፒኦ ሲያሲይዙ ቫት የሚጠይቁትን ጨምሮ መሙላትና ማሰያዝ አለባቸው፡፡ የሚጠይቁዉ የአንድ ወይም በጥቅል (ሎት) የሚገዛዉ እቃ እንጅ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ዉስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 350 (ሶስት መቶ ሃምሳ ብር) የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  8. ቅዳሜ ለዩኒየኑ የሥራ ቀን ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ጨረታው ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን የንግድ ፈቃዱ የማይጋብዝ ካልሆነ በስተቀር ከሎት አንድ እና አራት ወጭ ያሉትን ግን ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት ይችላሉ፡፡
  12. አሸናፊው ያሸነፈዉን እቃ በእራሱ ትራንስፖርት አጓጓዞ ሊወስድ እና ሊያቀርብ ነዉ፡፡ ማንኛዉም ወጭ አሸናፊዉ ይሸፍናል፡፡ የሚገዙትን ሆነ የሚሽጡ ማንኛዉም እቃዎች መጠንና (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡ አሸናፊዉ የሚለየዉ በተናጠል ይሆናል፡፡
  13. አሸናፊዉ ያሸነፈበትን ግዥዎች /ሽያጭ/ በፍትህ ዉሉ ከተመረመረ (ከተመዘገበ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊዉ ይከፍላል፡፡ ሰብሉን ለማንሳት የሚያሰፈለጉ ማንኛውም የወዛደር ማሰጫኛ እና የትራንሰፓርት ወጭዎች አሽናፊ የሚሽፍን ይሆናል፡፡
  14. ሰብሉ የሚገኝበት ቦታ ባ/ዳር ከተማ ከዩኒየኑ መጋዘን የሚገኝ ሲሆን ጥራቱን በአካል በማየት መሙላት ይችላሉ፡፡
  15. በዚህ ያልተጠቀሱ ሃሳቦች ቢኖሩ በህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  16. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 11 59 05 34 /058 320 16 70 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here