በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
55

በኢየሩሳሌም የሕፃናት እና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት የባሕር ዳር እና አካባቢዉ የማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም ጽ/ቤት ያገለገሉ እና አዳዲስ የዉሃ ቧንቧዎችን እና መገጣጠሚያዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን እንዲሁም ከእንጨትና ብረት የተሰሩ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን በማሟለት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 10፡00 ድረስ የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ የመወዳደሪያ ሰነድ ከባሕር ዳር እና አካባቢዉ የማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም ጽ/ቤት በመዉሰድ የሚሰጡትን ዋጋ ሞልተዉ ለባሕር ዳር እና አካባቢዉ የማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም ጽ/ቤት አፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ማራኪ ቀበሌ አባይ ማዶ ከአጋር ሎጅ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘዉ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  2. ለጨረታዉ ማስከበሪያ የጨረታ ዋጋዉን 20 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታዉ አሸናፊ ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለጽለት ዕለት ጀምሮ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ከፍሎ እቃዎቹን ማንሳት አለበት፡፡ በተጠቀሰዉ ቀን ዉስጥ ካላነሳ የጨረታዉ አሸናፊ ያስያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሁኖ ንብረቶቹ ለ2ተኛ አሸናፊ የሚሸጡ ይሆናሉ፡፡
  4. ሁለት እና ከዚያ በላይ ተጫራቾች ለአንድ ዕቃ እኩል ዋጋ በመስጠት አሸናፊ ቢሆኑ እንደገና በማወዳደር አሸናፊዉ ይለያል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  6. አሸናፊዉ ተጫራች ያሸነፈዉን ንብረት በጨረታ ሰነዱ በተጠቀሰዉ መጠን ልክ ሙሉ በሙሉ ማንሳት ይጠበቅበታል፡፡
  7. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉት ንብረት ዋጋ ሰነዱ ላይ ያለ ስርዝ ድልዝ በመሙላት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ስም እና ሙሉ አድራሻቸዉን በመጥቀስ ከነሐሴ 4/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም ድረስ ለድርጅታችን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታዉ ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ  3፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም ጽ/ቤቱ ዉስጥ ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን ያልገዛ ተጫራች በጨረታዉ ሊሳተፍ አይችልም፡፡ በኮፒ ጨረታ ሰነድ መጠቀም አይቻልም፡፡
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ የሚሞሉት በድርጅታችን በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ብቻ ነዉ፡፡
  10. በእርሳስ የተሞላ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም፡፡
  11. በጨረታዉ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የሕጋዊ ወኪሉ ፊርማ እና አንዲሁም ተጫራቹ ድርጅት ከሆነ ፊርማ እና ማህተም ከሌለበት ዋጋ አይኖረዉም፡፡
  12. አንድ ተጫራች ከአንድ ጊዜ በላይ የጨረታ ሰነድ ማስገባት አይችልም፡፡
  13. ማንኛዉም ተጫራች በጨረታዉ ተካፋይ ሁኖ ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ የሰጠዉን ዋጋ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፡፡
  14. አንድ ተጫራች አሸናፊነቱ የሚገለፀዉ የሚለየዉ በድምሩ ሳይሆን ለእያንዳንዱ ዕቃ ባቀረበዉ ዋጋ ብቻ ነዉ፡፡
  15. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  16. ተጫራቾች ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 30 96 44 59 /09 18 76 49 03 ደዉለዉ ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን በወሰደዉ ቅጽ ላይ ከሞላ በኃላ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ በጨረታዉ ሰነድ ላይ ስምና ፊርማ በሚለዉ ክፍት ቦታ በሙሉ መፃፍና መፈረም ግዴታ ነዉ፡፡

በኢየሩሳሌም የሕፃናት እና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት

የባሕር ዳር እና አካባቢዉ ማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here