የሰሜን ወሎ ዞን የጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከመደበኛ በጀት ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ እና ሎት 2. የጽዳት እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸዉ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ሎት በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት በማቅረብና ማጓጓዝ፣ የመጫኛና የማዉረጃ ወጭዉን በራሳቸዉ በመሸፈን አለባቸዉ ሁሉንም ንብረቶች በጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሚገኙ ንብረት ክፍሎች ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውል በመውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉበትን እቃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸው ማህተም ስምና ፊርማ በሚነበብ መልኩ መፃፍና በየገፁ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ከፒ ማድረግ በየሎቱ በፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- ውድድሩ በጠቅላላ ድምር ዋጋ በሎት መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች ስለሚያቀርቧቸው እቃዎች ትክክለኛነቱን እና በተጠየቀው ስፔስፊኬሽን መሰረት ስለመቅረቡ በጥራት አረጋጋጭ ባለሙያ ተረጋግጦ መስሪያ ቤቱ የሚረከብ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በሰሜን ወሎ ዞን በጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በመምጣት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ከነማስረጃዎቹ በታሸገ ፖስታ በድርጅትዎ ማህተም ተረጋግጦ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሁሉም ሎቶች ለተከታታይ 15 ቀን ቆይቶ በ16 ተኛው ቀን 5፡00 ላይ ታሽጎ 5፡30 ላይ በግዥ ንብረት አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ ሁሉም ጨረታዎች ወደ ቀጣይ የሥራ ቀን ተሸጋግሮ 5፡00 ታሽጎ 5፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ማስተካከያ ጥያቄ ካላችሁ ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ በደብዳቤ ማሳወቅ አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሚወዳደሩበት ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ ብር 40,000 (አርባ ሽህ ብር) ሎት 2. የጽዳት እቃ ብር 4,000 (አራት ሽህ ብር) በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲፒኦ ኦርጅናሉን በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ከታወቀ በኋላ አሸናፊው ውል ከወሰደ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ይለቀቃል፣ አሸናፊዉ የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲፒኦ እና በሁኔታ ላይ ባለተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ኦርጅናሉን በማስያዝ በጉ/ወ/ፍትህ/ጽ/ቤት በኩል ውል መውሰድ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ያሸነፈውን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ሳያስረክብ ክፍያ ቢጠይቅ ወይም እቃው በገበያ ላይ የለም የሚል ምክንያት መ/ቤቱ አያስተናግድም፡፡ ነገር ግን እቃዎቹን ሙሉ በሙሉ ካስረከበ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈፀማል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የተሳሳተ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 431 07 36 ወይም 033 540 07 21 ደውለው ወይም የጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመምጣት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጉባላፍቶ ወርዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ወልድያ

