የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት የመኪና ጎማ ከነካለመዳሪው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዥ እና ንብረት አስተዳዳር ቡድን በቢሮው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከነሐሴ 11/2018 ዓ/ም እስከ ነሐሴ 25/2018 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሶስተኛ ፎቅ ግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል ጠ/ፍ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 02 56 65 /09 08 64 99 67 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት
ባሕር ዳር

