ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
35

የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ የባዮጋዝ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ዩኒት ዶም ፓይፕ እና ባዮ ጋዝ ምድጃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን በየንግድ ዘርፉ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና አስፈላጊ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 140,000 (አንድ መቶ አርባ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  2. በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ባሕር ዳር ህንጻ የባዮጋዝ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ዩኒት ቢሮ ቁጥር 406 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት  መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች ለመወዳደር የመወዳደሪያ ሰነዶችን ሲመልሱ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማ፣ አድራሻ እና የመወዳደሪያ ዝቅተኛ ዋጋ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባዮጋዝ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ዩኒት  ቢሮ  406 ይከፈታል፡፡
  4. ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የተወሰደው እርምጃ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
  5. የማቅረቢያ ጊዜ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ25 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ርክክብ የሚፈፅም ይሆናል፡፡ ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  6. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 04 78 ዘወትር በሥራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ ቀበሌ 05 ባሕር ዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ወይም ፕሮቴክሽን ሀዉስ ህንፃ ጎን፣ ኢትዮጵያ መድን ድርጅት ህንጻ ባዮጋዝ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ዩኒት ቢሮ ቁጥር 406 ነው፡፡

በአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ

ባሕርዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here