ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
30

አባይ ኮነንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ማርዛ መስኖ ፕሮጀክትን እና እነነዘር አፈር ግድብ ፕሮጀክትን ከንዑስ ሥራ ተቋራጮች ጋር ውል በመያዝ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት በዘርፉ የተሰማሩ ደረጃ -4 እና ከዚያ በላይ WC ወይም GC የሆኑ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ንዑስ ሥራ ተቋራጭ መካከል አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. ንዑስ ተቋራጮች በ2018 ዓ.ም በዘርፉ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰነድ፣ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት እንዲሁም የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ከኩባንያችን ጋር በሰብ ኮንትራት ውል ወስደው በሥራ ላይ ያሉ ተቋራጮች ውል የወሰዱበትን ሥራ ሳይጨርሱ በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡፡
  3. ንዑስ ተቋራጮች የጨረታ ዋጋቸውን ሲሞሉ ለሥራው የሚያስፈልገውን ማንኛውም የሰው ሀይል ወጪ እና ማሽን ያገናዘበ እንዲሆን ታሳቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የሥራው ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሥራዎች ለእያንዳንዱ ፕሮጀክት ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋጋጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guaraantee) በአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ ማህበር ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ንዑስ ተቋራጮች የጨረታ ሰነዱን በባሕር ዳር ጣና ክ/ከተማ፤ ህዳሴ ቀበሌ አመልድ ጋራዥ በሚገኘው ከኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 19 ግዥና አቅርቦት ሥራ ክፍል ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም በኩባንያው ዌብ ሳየይት https://www.abayconstruction.org.et/auction-bid ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ብቻ የሚቆይ ሲሆን በ15 ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡30 በባ/ዳር ጣና ክ/ከተማ ህዳሴ ቀበሌ፣ አመልድ ጋራዥ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታው መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተማሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ ማህበር የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለ ጨረታው በጽሁፍም ሆነ በስልክ ማብራሪያ (Clarification) መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 09 18 76 41 70 /09 12 99 33 21 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አባይ ኮነንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here