ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
5

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የዘር አሰባሰብና የቀጥታ ዘር ግብይት ዘር ለማሰራጨት የተለያዩ ምርጥ ዘሮችን ከተለያዩ ወረዳዎች ወደ ዘር ማበጠሪያና ማከማቻ ጣቢያዎች ለማጓጓዝ፣ የሰብል ጥበቃ ቁሳቁስና የተለያዩ ኬሚካሎች ግዥ፣ የዘር ማበጠሪያ ማሽን መለዋወጫ ግዥ፣ የላብራቶሪ ማቴሪያል ግዥ፣ የዘር ማሰባሰቢያ ጆንያ፣ የዘር ማሸጊያ ከረጢት ለማሳተም እና ለዘር ማሰባሰብ የሚዉሉ እቃዎች፣ የኤሌክትሪክ እና የፈርኒቸር እቃዎች ለማስጠገን እና የተለያዩ ለዘር የማይሆኑ ሰብሎች የተለያዩ ብጣሪዎች፣ ያገለገሉ ጆንያዎችን እና ያገለገሉ እቃዎችን ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-

  1. የንግድ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር/ቢሮ/ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የዘመኑን የመንግስት ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የመኪና ባለቤትነት ማረጋገጫ እና የመጫን ችሎታ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
  3. የማበጠሪያ ማሽን መለዋወጫ ለማቅረብ ፈቃድ የተሰጠዉና ከ2 ወር ባልበለጠ ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. የደረቅ ጭነት ማመላለሻ መኪኖች ያሉትና የመኪኖችን የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ከዋናው ጋር
    የተረጋገጠ ኮፒ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም ሲጠየቅ ዋናውን ሊብሬ ማቅረብ የሚችል፣
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፣
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርኘራይዙ ዋና መስሪያ ቤት /ባሕር ዳር/ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
  9. የተለያዩ ንፁህ ሰብሎች የምግብ እህሎች በተመለከተ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸዉ፡፡
  10. ግዥዉን ባሕር ዳር ዋናዉ መስሪያ ቤት መጋዘን መድሐኒዓለም አካባቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሌሎች ዝርዝሮችን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባሕር ዳር ከተማ በአለ በጅምላ ግቢ ዉስጥ በሚገኘዉ በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ 10ኛው ቀን ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  12. ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀዉ ዉስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን እስከ 50 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  13. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582266002 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0583208415 ወይም 0918016935 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here