ወገን የሕጻናት እና እናቶች መርጃ ድርጅት በኢፊዲሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ፈቃድ ቁጥር 0712 ተመዝግቦ ከመጋቢት 1/2012 ዓ/ም ጀምሮ በሥራ ላይ ያለ ሀገር በቀል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅታችን እ.ኤ.አ 2026 የበጀት ዓመት ሒሳብ ለማስመርመር (ኦዲት) ስለፈለገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የኦዲት ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የሙያ ማረጋገጫ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- INPAS የኦዲት አሰራርን የሚተገብር፡፡
- የፐብሊክ ኦዲተርነት ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- ከፌደራል ወይም ከክልል ኦዲት መስሪያ ቤት የዚህ በጀት ዓመት የታደሰ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- በኦዲት ብቁ የሥራ ልምድ ባለሙያ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ ማረጋገጫ ያላቸው፡፡
- በበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት ኤጀንሲ በኦዲተርነት የተመዘገቡ፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለአገልግሎቱ የምታስከፍሉትን ዋጋ እና ሥራዉን አጠናቃችሁ የምታስረክቡበትን የቀን ገደብ የሚገልጽ ሰነድ በማያያዝ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ወደ ቢሮችን በመምጣት ሰነዳችሁን ማስገባት የሚችሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 058 111 22 30 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ ፦ ጎንደር ቀበሌ 01
ወገን የሕጻናት እና እናቶች መርጃ ድርጅት

