በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ዲስክ ቶኘ ኮምፒተር እና ኘሪተር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1 እስከ 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የአገልግሎት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሰስት መቶ) ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 315 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ወይም መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 315 ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ወይም መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ ብር 20,000 (ሃያ ሽህ ) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በ11ኛው ቀን አስከ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 315 በ11ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በ3.00 ተዘግቶ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 315 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 9644/058 220 9646 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ
ባህርዳር

