ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
22

የአብክመ ማሽነሪ ኢንጅነሪ ግሩፕ (ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጅ ልማት ኢንተርፕራይዝ) ለባህር ዳር ፍሌክሴብል ፋውንደሪ ፋብሪካ የደህንነት ካሜራና አክሰሰሪዎችን  እና የእጅ  ዋጋን ጨምሮ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ዝቅተኛ ዋጋ  አሸናፊ ከሆነው ተጫራች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ  ይጋብዛል፡፡

  1. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና በዘርፉ  የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ይህን የሚያረጋግጥ የምስክር  ወረቀት ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የስራውን  ሙሉ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  1. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ፣ የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 60,000 (ስልሳ ሽህ ብር) ተቀባይነት ባላቸው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያዉ ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያዉ ሰነድ ካለበት ፖስታ ዉስጥ አስገብቶ በማሸግ በተገለጸው የስራ ቀናት ዉስጥ ቢሮ ቁጥር 34 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የቀድሞው ግብርና ሜካናይዜሽን ቢሮ ባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ በሚገኘው ማሸነሪ ኢንጅነሪግ ግሩፕ (የአብክመ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጅ ልማት ኢንተርፕራይዝ) ቢሮ ቁጥር 33 በመቅረብ ማስታወቂያው በጋዜጣ ወይም በሌሎች መገናኛ ብዙሃን በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ  ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ወይም በሌሎች መገናኛ ብዙሃን በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሁኖ ይቆይና፤ በ21ኛው ቀን 4፡00 ታሸጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀድሞው ግብርና ሜካናይዜሽን ባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ በሚገኘው የአብክመ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጅ ልማት ኢንተርፕራይዝ ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡ በተቋሙ የስራ ቀን ቅዳሜን ይጨምራል፡፡
  3. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ይህም ሲሆን ጨረታው በመሰረዙ ምክንያት ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ ኢንተርፕራይዙ ሃላፊነት አይወስድም፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 33 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 69 88/058 320 6131  በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ማሽን ኢንጂነሪንግ ግሩፕ (የብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጅ ልማት ኢንተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here