ማኦ ኮሞ ብሔራዊ ፓርክ

0
20

የማኦ ኮሞ ብሔራዊ ፓርክ በምእራብ ኢትዮጵያ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ነው የሚገኘው፡፡ ቀጣናው ብሔራዊ ፓርክ ሆኖ የተመሰረተው በ2016 እ.አ.አ ሲሆን የምእራብ ኢትዮጵያ ስነም ህዳሮችን ለመጠበቅ ከተቋቋሙ አዳዲስ የክልል  ፓርኮች አንዱ ነው፡፡

የፓርኩ ስፋት 2330 ካሬ ኪሎ ሜትር ተለክቷል፡፡ ለፓርኩ ቅርብ የሆነው የክልሉ ዋና ከተማ አሶሳ ሲሆን 150 ኪሎ ሜትር ርቆ ነው የሚገኘው፤ ፓርኩ ማኦ ኮሞ የሚለውን ስያሜውን ያገኘው ከቀደምት ነባር የቀጣናው ኗሪ ከሆኑት ማኦ እና ኮሞ ብሔረሰቦች ነው፡፡

የፓርኩ መልካምድራዊ አቀማመጥ ዝቅተኛ ማለትም ቆላማ ቦታዎች፣ የደለል ንጣፍ እና የወንዝ ሸለቆዎች አሉት፡፡ የደለሉ ቀጣና የሞቃታማ ደን መጋቢ ነው፡፡ የጅረቶች እና ወንዞች መውረጃ ሸለቆዎች እና ገደላ ገደሎችን ቀርፆ የፓርኩ አካል አድርጓቸዋል፡፡

ፓርኩ ከእፅዋት የቆላማ ደንን ለብሷል፡፡ በደኑም እስከ 30 ሜትር ቁመት ያላቸው ዛፎች በብዛት ተሰድረው ይገኛሉ፤ በዛፎቹ ስር የሚገኘው መሬትም በቁጥቋጦዎች የተሸፈነ ነው፡፡

ፓርኩ ከዱር እንስሳት – ጐሽ፣ አሳማ፣ ጥቁር እና ነጭ ዝንጅሮ ፣ የሜዳ ፍየል፤ ከአዳኝ የዱር እንስሳት ጅብ፣ ነብር፣ የዱር ውሻ መገኘታቸውን ድረገፆች አስፍረዋል፡፡

የፓርኩ መገኛ ቀደምት ወይም ጥንታዊ የፕሪካም ቤሪያን ንጣፍ ወይም ንብብር የሚበዛው በመሆኑ የወርቅ ማእድንን የያዘ ነው፡፡ ይህም አነስተኛ የግል ማእድን አውጪ ቆፋሪዎች ያለ ቁጥጥር እንዲሰማሩ እድል ፈጥሮ በቀጣናው የብዝሃ – ህይወት ቀጣይነት ላይ ስጋትን ደቅኗል፡፡

የፓርኩ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ1200 እስከ 2000 ሚሊ ሜትር ተመዝግቧል፡፡ ዋናው የዝናብ ወቅት ከግንቦት እስከ ጥቅምት አማካዩ ሙቀቱ ደግሞ ከ20 እስከ 35 ዲግሪ ሼልስየስ ተለክቷል፡፡

ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ኢንተርናሽናል ፓርክ ዶት ኦርግ፣ ናሽናል ፓርክ ዶት ኦርግ እና ጐግልን ተጠቅመናል፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here