ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
15

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 2. የመኪና መለዋዎጫ እቃዎች፣ ሎት 3. የመኪና ጎማ፣  ሎት 4. የውሃ እቃ አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ከገቢዎች የታክስ ክሊራንስ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤታችን ረዳት ገንዘብ ያዥ የስራ ክፍል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር ለሎት 1. ብር 40,000 (አርባ ሽህ ብር)፣ ለሎት እና 3. ለእያንዳንዱ ብር 50,000 (ሃምሳ ሽህ ብር)፣ ለሎት 4. ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዛ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዝብ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ገ/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ ቢሮ ቁጥር 1 በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ያወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎችን ወረዳው ድረስ በራሱ ትራንስፓርት ወጭ ማቅረብ የሚችልና ለፍትሕም ሆነ ለማንኛውም አገልግሎት የሚከፈለውን ወጭ በራሱ የሚችል፡፡
  13. የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴ የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) ማስተካከያ በሚሰራበት ወቅት ተጫራቾች በመክፈቻ ወቅት ካቀረቡት የንባብ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር ልዩነቱ ወደ ላይም ሆነ ወደ ታች ከ3 በመቶ ከበለጠ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
  14. የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) በግዥ ፈጸሚው መ/ቤቱ ባለሙያ ከሚስተካከለው ውጭ በተጫረቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ ሆነ በጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቾች ከጨረታ በውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
  15. መስሪያ ቤቱ ጨረታ አሸናፈውን በጥቅል ዋጋ ይለያል፡፡
  16. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ አቤቱታ (ቅሬታ) ካላቸው በተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውጭ የመጣ ቅሬታ መ/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  17. መ/ቤቱ ከአሸናፊ ድርጅቱ ያሽነፋቸውን እቃዎች 20 በመቶ ከውል በፊት የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. እቃዎች በባለሙያ እየተረጋገጡ ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
  19. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል፣ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት  ይሆናል፡፡
  20. አሸናፈው ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ መጥቶ ውል በመያዝ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  21. ከአሸናፊው ድርጅት 3 በመቶ የቅድመ ግብር የሚቆረጥ ይሆናል፡፡
  22. ግዥ ፈጻሚው አካል ግዥውን ለመገምገም፣ ለማጽደት አቤቱታ ቢነሳ ለማስተናገድ እና ከአሸናፊ ድርጅቱ ጋር ውል እስከሚገባ ድረስ የመጫረቻ ሰነዱ ጸንቶ የሚቆይበት ለ40 ቀን ይሆናል፡፡
  23. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ 28 ቀናት ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
  24. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 664 04 64 /002 በመደወል ዝርዝር መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here