የቋሚ ቅጥር ማስታወቂያ

0
4

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች ያለውን ክፍት የስራ መደብ  ተፈላጊ ችሎታውን ከሚያሟሉ ስራ ፈላጊዎች መካከል በቋሚ ቅጥር  አወዳድሮ በመቅጠር ማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

ተ.ቁ የሥራ መደቡ መጠሪያ ደረጃ የመ/መ/ቁ ደመወዝ ብዛት የሚሰራበት የስራ ክፍል የሥራ ቦታ ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት አግባብ ያለዉ የስራ ልምድ
1.      1 የጉምዝኛ ቋንቋ  ሪፖርተር 2

 

9  

አሚ-842

 

በኮርፖሬሽኑ የደመወዝ

ስኬል

መሰረት

01 ጉምዝኛ ዝግጅት ክፍል ባህር ዳር በጋዜጠኝነት፣በተግባቦት፣ በስነ ጽሁፍ፣በቋንቋ፣በቲያትሪካል አርት የሰለጠነ/ች የአማረኛ እና የጉምዝኛ ቋንቋ መስማት ፣መናገር፣ማንበብና መጻፍ የሚችሉ፡፡

 

በመጀመሪያ ዲግሪ 0 ዓመት የስራ ልምድ

 

     ማሳሰቢያ፡–

  • የምዝገባ ቀን በበኩር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
  • አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • አመልካቾች በእምነት ማጉደል ፣በማጭበርበር ወይም በስርቆት ወንጀል ተከሰዉ ስልጣን ባለዉ አካል ተፈርዶባቸዉ የመቀጠር መብታቸዉን እንዲጠቀሙ ስልጣን ያለዉ ፍርድ ቤት የወሰነበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ኦርጅናሉን የትምህርት ማስረጃ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ከተጠቀሰዉ አግባብነት ያለው የትምህርት ዝግጅት ውጭ ለምዝገባ የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተቀባይነት አይኖራቸዉም፡፡
  • መልካም ስነ-ምግባር ያለው/ላት፣ ከማንኛውም ደባል ሱስ የፀዳ/ች እና ጥሩ ስብዕና ያለው/ላት፡፡
  • በተመዘገቡበት የስራ መደብ ለምን ተቀጥረው መስራት እንደፈለጉ በጽሁፍ ገልፀው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • አመልካቾች የሙያ ብቃት በሚያስፈልጋቸው የትምህርት ዝግጅት የብቃት ማረጋገጫ በማስታወቂያው በተጠየቀው የትምህርት ደረጃ ልክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • በዚህ ማስታወቂያ ተወዳድሮ ያለፈ ከወንጀል ነፃ መሆኑን ከሚኖርበት ቀበሌ አስተዳደር ወይም የህግ አካላት ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  • በተጠቀሰው የትምህርት መስክ የሙያ ብቃት ምዘና የማይሰጥ ከሆነ ከሚመለከተው ተቋም የሙያ ብቃት አለመጀመሩን ማስረጃ ካቀረቡ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
  • ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ  በሌላ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
  • በጽኑ እስራት በሚያስቀጣ ወንጀል ተከሶ የተፈረደበትና ከእስር የተፈታ እንዲሁም በዲሲፒሊን ጉድለት ምክንያት ከስራ የተሰናበተ በኮርፖሬሽኑ ሊቀጠሩ አይችሉም፡፡
  • አመልካቾች የምትመዘገቡበት ሊንክ በዌብሳይታችን amharaweb.com ማግኘት ትችላላችሁ ወይም ሊንኩን በመጫን ይመዝገቡ  https://forms.gle/GtoPyCSYZNL55Y4i9 መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 226 50 07 ባህር ዳር ይደውሉ፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባሕር ዳር

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here