የደልጊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሆስፒታሉን ህንጻ የግንባታ እና የእድሳት ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ከደረጃ ስድስትና ከዛ በላይ የግንባታ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የስራው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋጋጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ወይም የሆስፒታሉን የግንባታ እድሳትና ጥገና ጠቅላላ ዋጋ 1በመቶ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሆስፒታሉ ህጋዊ ደረሰኝ ተቆርጦ ከሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደልጊ ሆስፒታል
በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመጋቢት 28/2018 ዓ.ም እስከ መጋቢት 12/2018 ዓ.ም ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆያል፤ ጨረታዉ በ16ኛው ቀን 3፡00 ላይ በሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። 3፡30 ላይ ሳጥኑ ይታሸጋል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደልጊ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም 4፡00 ላይ ይከፈታል ፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ) ደልጊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ድረስ
መጥተዉ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ
ያላስዘና ውል ያልፈፀመ እንደሆነ ግዥ ፈጻሚው አካል የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት ይኖረዋል።
- ክፍያው የሚፈፀመው በውሉ መሰረት ይሆናል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
- በጨረታ ማስታወቂያው ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በመመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደልጊ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊዉ የሚለየዉ በሎት ወይም ዝቅተኛ ለግንባታ በሚያስፈልጉ አጠቃላይ የማቴሪያል እና የእጅ ዋጋ ጥቅል ድምር ዉጤት ነዉ፡፡
የደልጊ ሆስፒታል

