በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አገልግሉት የሚውሉ ጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪና ጎማ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሀጋዊ ንግድ የ2018 ዓ.ም ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የእቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 102 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከረበያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ፋ/ን/አ ዳይሮክቶሬት ቢሮ ቁጥር 107 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀናት ከረፋዱ 3፡00 ድረስ በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 3፡05 ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ቁጥር 107 በ16ኛው ቀን በ3፡30 ይከፈታል፡፡ ጨረታ በሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 22 70 /058 226 21 77 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ

