ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
47

የጨረታ ቁጥር፦ አብክመ አብብማቴልድ/የት-ል-ሽ-01/06/2018

የአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝ በስሩ የያዛቸውን የተለያየ የፈረስ ጉልበት ያላቸውን የኬዝ ባለ 127 እና 110 እንዲሁም ማሲ ፈርጉሰን /MASSY FERGUSEN/132 የፈረስ ጉልበት ትራክተሮች የትራክተር ማረሻ አቦሎ /Aboo/፣ የበቆሎ መፈልፈያ ማሽን እና የብረት ሸልፍን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የኬዝ ባለ 127 እና 110 የፈረስ ጉልበት ማሲ ፈርጉሰን /MASSY FERGUSEN 132 የፈረስ ጉልበት የትራክተር ማረሻ አቦሎ (Abollo)፣ የበቆሎ መፈልፈያ ማሽን እና የብረት ሽልፎች ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሠነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 31 በመክፈል ከመጋቢት 28/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 19/2018 ዓ/ም 4፡00 ድረስ የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን የኬዝ ባለ 127 እና 110 የፈረስ ጉልበት፣ ማሲ ፈርጉሰን (MASSY FERGUSEN) 132 የፈረስ ጉልበት ያላቸው ትራክተሮች፣ የትራክተር ማረሻ አቦሎ (Aboo) ፣ የበቆሎ መፈልፈያ ማሽን እና የብረት ሸልፍ የሞሉትን የጠቅላላ ድምር ዋጋዉን 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም 60 ቀን ያላነሰ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በአንድ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ የአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝ ስም በማሰራት በአንድ ፖስታ ብቻ በማሸግ በተዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዋጋ የሞሉበትን ገጽ ብቻ ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 13 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከመጋቢት 28/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 19/2018 ዓ/ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 13 ሚያዚያ 19/2018 ዓ/ም 4:00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ሚያዚያ 19/2018 ዓ/ም 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡ የኬዝ ባለ 127 እና 110 የፈረስ ጉልበት፣ ማሲ ፈርጉሰን /MASSY FERGUSEN 132 የፈረስ ጉልበት ያላቸው ትራክተሮች፣ የትራክተር ማረሻ አቦሎ (Abollo) ፣ የበቆሎ መፈልፈያ ማሽን እና የብረት ሸልፎች በተገለፀዉ ቦታ ከመጋቢት 28/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 19/2018 ዓ/ም 4፡00 ድረስ ንብረቶች ባሉበት ቦታ በመሄድ በአካል ማየት ይችላሉ፡፡ ርክክብ የሚፈጸመዉም በጨረታ ሠነዱ ላይ በተቀመጠዉ ቦታ ነዉ፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነዉ በተናጠል በተሰጣቸው መለያ ቁጥር መሰረት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች በፖስታቸዉ ላይ ስም ከነአያት፣ ፊርማና ስልክ ቁጥር መፃፍ አለባቸዉ፡፡
  10. ከጨረታው መነሻ ዋጋ በታች ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  11. በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) የጨረታው ውጤት በኢንተርፕራይዙ የማስታወቂያ ቦርድ ላይ ለ3 ተከታታይ የስራ ቀናት ተለጥፎ ከቆየና ቅሬታ ካለም ቅሬታው ቀርቦ ከተፈታ በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን አሸናፊ ለሆኑት ተጫራቾች ደግሞ አሸናፊ የሆኑበትን ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ ከፍለው እንዳጠናቀቁ የሚመለስ ይሆናል፡፡
  12. በጨረታው ውጤት ቅር የተሰኘ ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ውጤት በጊዚያዊነት ይፋ በሚደረግበት ሽያጭ ቦታና በዕለቱ እንዲሁም ውጤቱ በኢንተርፕራይዙ የማስታወቂያ ቦርድ ላይ ከተለጠፈበት እለት ጀምሮ ባሉት 3 (ሶስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን በጽሁፍ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  13. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን እቃ ዋጋ ኢንተርፕራይዙ በሚያሳውቀው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ ነገር ግን የጨረታው አሸናፊ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ገንዘቡን ገቢ ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለኢንተርፕራይዙ ገቢ ሆኖ ንብረቱ ወይም እቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  14. በጨረታ ሂደቱ አሸናፊ የሆነው ድርጅት (ግለሰብ) አሸናፊ ለሆነበት ንብረት የሚጠበቅበትን ክፍያ ፈጽሞ ሲቀርብ እንደ አስፈላጊነቱ ወይም ኢንተርፕራይዙ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው የገዥና የሻጭ ውል የመዋዋል ግዴታ ይኖርበታል፡፡ ንብረቶቹንም በናሙና እይታ ወቅት ባየውና ተስማምቶ ዋጋ ባቀረበውና አሸናፊ በሆነበት ሁኔታ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ የመረከብ ግዴታ አለበት፡፡
  15. አሸናፊው ግለሰብ ወይም ድርጅት ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ባደረገ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ እቃውን የመረከብ ግደታ አለበት፡፡
  16. በጨረታው የተሸጠው እቃ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ካልተነሳ ጠቅላላ ካሸነፈው ገንዘብ ላይ ቀኑ ካለፈበት ቀን ጀምሮ በየቀኑ1 በመቶ እየታሰበ የመጋዘን ኪራይ የመክፈል ግደታ አለበት፡፡
  17. በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ያላስያዙትን ተጫራቾች ኢንተርፕራይዙ ከጨረታው ይሰርዛል፡፡
  18. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  19. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 221 99 87 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- ባሕር ዳር ከተማ ከቀድሞው ግብርና ሜካናይዜሽን ቢሮ ባሕር ዳር ዙሪያ ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ ባሕር ዳር ቀበሌ 17 በሚገኘው አብክመ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጅ ልማት ኢንተርፕራይዝ ይገኛል፡፡

አብክመ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጅ ልማት ኢንተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here