የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
46
ተ/ቁ የተበዳሪ ስም የንብረት አስያዥ ስም አበዳሪ ቅርንጫፍ ለጨረታ የቀረበው ንብረት መግለጫ የጨረታ መነሻ ዋጋ ጨረታ የሚከሄድበት ጨረታ የወጣው
ለጨረታ የቀረበ ንብረት

አገልግሎት

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

 

የካርታ ቁጥር/የይዞታ መላያ ቁጥር የቦታው ስፋት በካ/ሜ

 

ቀን ሰዓት ቦታ
1  ዘገየ ይታየው እና ወርቃለም በሪሁን  ዘገየ ይታየው እና ወርቃለም በሪሁን ቻግኒ  ወተት ማቀናበሪያ

 

ቻግኒ ከተማ 01 ቀበሌ

 

 141/2008  250ካ/ሜ ብር 1,284,931.63 29-08-2018 ከ4፡00-6፡00 እንጅባራ ዲስትሪክት 3ኛ ፎቅ የስብሰባ አደራሽ

 

የመጀመሪያ

               

የሀራጁ ደንቦች

  1. ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በፀደይ ባንክ አ/ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የፀደቀ የድርጅቱ መመሥረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፣ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ቃለ ጉባኤ ወይም ሕጋዊ የውክልና ሠነድ ማቅረብ አለበት፡፡
  3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃልሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሜ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጭዎች ይከፍላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት ጨረታው ከመከሄዱ በፊት አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታው ቦታ በእንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ በሚገኘው የፀደይ ባንክ አ.ማ እንጅባራ ዲስትሪከት 3ኛ ፎቅ  በሚገኘው የስበሳባ አዳራሽ ውስጥ ይሆናል፡፡
  8. ባንኩ ለሽያጭ ያቀረበውን ንብረት የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ ወይም በከፊል ብድር ሲሆን አሸናፊ በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሰረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ከሟላ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል፡፡
  9. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት 30 ዳቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
  10. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብደቤ በፁኁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
  11. ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብደቤ ይጽፋል፡፡
  12. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-058 227 07 08 እና 09 18 74 55 34 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ፀደይ ባንክ አ/ማ

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here