በምሥራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን የደብረ ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ/ን/አስ/ቡድን ከ2018 የመደበኛ በጀት ለትምህርት ጽ/ቤት በትግል ፍሬ ትምህርት ቤት የቅድመ መደበኛ መማሪያ ክፍል በዘርፉ ከተሰማሩ ደረጃ BC/GC 6 እና በላይ ከሆኑ ነጋዴዎች መካከል አወዳድሮ ለማስገንባት በተጨማሪ በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች የመኪና ጎማ እና ከለመዳሪያ እንዲሁም በሰቆጣ የቃልኪዳን በጀት የህንፃ መሳሪያ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች በዘርፉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች መካከል የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት እና ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት ከደብረ ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመቅረብ ለግንባታ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) እንዲሁም ለእቃ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ለግንቢታ በ31ኛው ቀን እንዲሁም ለእቃ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ይዘጋና በዕለቱ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾቸ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በጽ/ቤቱ የግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሞሉት የጨረታ ዋጋ ለግንባታ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሽህ ብር) ብቻ እንዲሁም ለእቃ በየሎቱ ብር 15000 (አስራ አምስት ሽህ ብር) በመ/ቤታችን መሂ1 ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡ ነገር ግን በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ በአድራሻ ለደብረ ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በማድረግ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ኦሪጅናል ለብቻው ኮፒውን ለብቻው አስፈላጊ ሰነዶችን በማሟላት በፖስታ በማሸግ እስክ 31ኛው ቀን እንዲሁም ለእቃ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ብቻ ቢሮ ቁጥር 08 ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የአሸናፊነት ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት፡፡ ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 10 በመቶ በመ/ቤቱ መሂ1 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡ ነገር ግን የግንባታ አሸናፊው ያሸነፈበት ዋጋ ከመሀንዲስ ግምት በታች የተጋነነ 25 በመቶ በታች ከሆነ ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 25 በመቶ በመ/ቤቱ መሂ 1 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ከአሰሪው መስሪያ ቤት ጋር ውል በመያዝ ወደ ስራ መግባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚያስቀምጠው አይነት ወይም ስፔስፊኬሽን መሰረት ሰነዳቸውን ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ውድድሩ በጥቅል በዋጋ ድምር ወይም በሎት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ሌሎች ያልተጠቀሱ አሰራሮች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና የክልል ገንዘብ ቢሮ በቁጥር አብክመ ገ/ቢ/ክቢ-01/02 በቀን 15/09/2014 ዓ.ም ባወጠው በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳድር ላይ በተደረገ የማሸሻያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 250 04 85 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደብረ ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

