የጨረታ ቁጥር 04
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ የቢሮው፣ የአብክመ ፕላን ኢንስቲቲዮት፣ የምዕራብ ቀጠና አራት ቅ/ጽ/ቤት፣ የከተሞች ምግብ ዋስትና እና ሴፍቲኔት ፕሮጀክት፣ UIIDP እና የኮንስትራክሽን ባለስልጣን የ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አላቂ፣ ቋሚ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡- ሎት 1. የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያ እቃዎች፣ ሎት 2. የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3. ፈርኒቸሮች፣ ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በመደበኛ እና በካፒታል በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ጋር ውል በመያዝ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- በዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብረ ከፍይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ከፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 27 /28/ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫረቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ገንዘብ ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ)፤ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በቢሮው ገንዘብ ያዥ ገቢ አድርገው ደረሰኝ ብቻ ማሲያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት 11፡30 ሰነዱን መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ የስባሰባ አዳራሽ በ16ኛው ቀን ይከፈታል፡፡ ቅዳሜ፣ እሁድ እና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 3:30 ታሽጎ 4:00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሎት 4 የተጠቀሱትን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ሲሞሉ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዶክመንት በተለያየ ፖስታ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ሁለት ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ያለምንም ሥርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይችላል፡፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 30 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 50 00 /058 226 61 80 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ

