ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
58

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን በመደበኛ ካፒታል በጀት እና በዩኒሴፍ በጀት እንዲሁም ለጉ/በ/ወ/ውሃ ጽ/ቤትና እንስሣት ፅ/ቤት በሰቆጣ በጀት ሎት 1 ለጉ/በ/ጤ/ጥ ጽ/ቤት በክምር ድንጋይ ከተማ የህዝብ መድሃኒት ቤት ለማስገንባት ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ፣ ሎት 2 በጉና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ጥገና በደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ  ጠቅላላ ስራ ተጫራቾች ማስጠገን፣ ሎት 3 የውሃ እቃዎች  እና የግንባታ እቃዎች እንዲሁም ሎት 4. ደሮ  እና የዶሮ መኖ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መስፈርቱን ሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ወይም የስራ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)ያላቸው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ግዥ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1. ብር 150,000፣ ለሎት 2. ብር 3,000፣ ሎት 3. ብር 8,000፣ ሎት 4. ብር 8,000 በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት  ወይም በጥሬ ገንዘብ  በመሂ 1 በማስቆረጥ በማስያዝ የሚችሉ፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ በጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 17 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለግንባታው ለተከታታይ 21 ቀን ሲሆን በ22ኛው ቀን ይከፈታል፡፡ የውሃ እቃ እና የግንባታ እቃዎች እንዲሁም የደሮ እና መኖ ለተከታታይ 15 ቀን ውሎ በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
  7. የዋጋ ዝርዝር መግለጫውን ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ሲሆን  በሚሞሉበት ሰዓት ስርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ መነካካት እና ሁለት አይነት ዋጋ ማስቀመጥ ከውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለሎት 1 የማይመለስ ብር 400  ለሌሎቹ  ደግሞ ለእያንዳንዳቸው  የማይመለስ ብር 120 በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. አሸናፊው ግንባታውን ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 25 በመቶ ከመሃንዲሱ ግምት ዝቅ ብሎ ከሞላ ኮስት ብሬክ እና ፕሮጀክት ወርክ እስኬጁል እንዲሁም በሞላው ዝቅተኛ ዋጋ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ አሸናፊነቱ ከተገለጸ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለበት፡፡ የተጋነነ ዝቅተኛ ሞልተው አሸናፊ ሆነው የግንባታ ተቋራጭ ውል ይዘው ወደ ስራ ሲገቡ ቅድመ ክፍያ አይፈቀድላቸውም፡፡ እንዲሁም የውል ማስከበሪያ የሞሉትን 10 በመቶ የነበረው ተሻሽሎ 25 በመቶ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ግዴታ ይሆናል፡፡
  10. ለግንባታ ፍይናስ ግምገማ ያለፈ ተጫራች ቢያንስ 3 እና በላይ ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ ከሂሳብ ስሌት ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 2.5 በመቶ ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚያ የበለጠ  ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡ ተጫራቾቹ ከ3 በታች ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ አንድ በመቶ ድረስ ብቻ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚያ በላይ ከሆነ ከውድድር ውጭ  ይሆናሉ፡፡
  11. አሸናፊው የሚለየው በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በዋጋ መሙያ መሰረት በሎት በጠቅላላ ድምር ብቻ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አሸናፊነቱን እንደተገለፀለት በ5 ተከታታይ ቀን ውስጥ ያሸነፉበት 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና  በጥሬ ገንዘብ  በመሂ 1 በማስቆረጥ በማስያዝ ውል መውሰድ ያለበት ሲሆን በወቅቱ ቀርበው ውል መውሰድ ካልቻሉ በግዥ መመሪያው 1/2003 መሰረት አስፈላጊውን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 251 02 26 ደውለው አስፈላጊውን መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here