ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
34

በማዕከላዊ ጎንደር በምሥራቅ በለሳ ወረዳ ጉሃላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል SUSAN Thomason butfet foundation በጀት የካርድ ክፍል ግንባታ፣ ሌሎች የጥገና ስራዎች የበርና ቁልፍ፣ የመስኮት፣ የቀለም፣ የውሃ እና የማዋለጃ ክፍል አልሙኒየም ፓርቲሽን በአጠቃላይ የመብራት ስራዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ይህን መስፈርት የሚያሟሉ በዘርፉ የተሰማራችሁ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፍ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የግንባታ ብቃት ደረጃ 9 ጀምሮ የሆናችሁ እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ፡፡
  2. ተጫራቾች ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በጎሃላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለዕለት ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት በሁለት ፖስታ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ከተፈረመበት ኦርጅናል ኮፒ በማለት በጉልህ ፖስታው ላይ በመፃፍ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ከሚያዚያ 19/2018 ዓ/ም እስከ ግንቦት 03/2018 ዓ/ም 11፡30 በተከታታይ ቀናት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጎሃላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተዘጋጀው ሳጥን ግንቦት 04/2018 ዓ/ም 3፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው፤ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን በዚህ ጨረታ የተወዳደራችሁ በአካል ወይም ተወካይበአካል ባይገኙም ጨረታው በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  6. ለፋይናንስ ግምገማ ያለፉት ተጫራቾች ቁጥር ቢያንስ 3 እና ከዚያ በላይ ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት ወይም (አርቲሜቲክ ቼክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበትን ልዩነት እስከ5 በመቶ ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  7. ለፋይናንስ ግምገማ ያለፉት ተጫራቾች ከ3 በታች ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት ወይም (አርቲሜቲክ ቼክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበትን ልዩነት እስከ አንድ በመቶ ድረስ ብቻ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚያ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
  8. አሸናፊው ተጫራች 30 በመቶ ቅድሚያ ክፍያና 25 በመቶ የውል ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ወይም በጥሬ ገንዘብ በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ የሚችል፡፡
  9. አሸናፊው የሚለየው በሎት በጥቅል ዋጋ ሲሆን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ሁሉም ለዕድሳት እና ለግንባታው የሚያስፈልጉ የግንባታ እቃዎች በተጫራቾች የሚቀርብ ሁኖ ሥራውን ይሰራሉ፡፡
  11. አሸናፊው የሚለየው የብቃት ደረጃቸው ከ9 ጀምሮ ካሉት ዝቅተኛ ዋጋ በቀረበው አሸናፈውን እንለያለን፡፡
  12. የሚሰራ የስራ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በማንኛውም ሰዓት በጎሃላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋን/አስ/ቡ/መሪ ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. አሸናፈው ድርጅት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምሥ/በ/ወ/ዓቃቢ ህግ ቢሮ ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችል፡፡
  15. ለበለጠ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 18 51 12 20 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ጠቅላላ የተዘረዘሩት ስራዎች (ግንባታው) በ60 ቀናት ውስጥ አጠናቆ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

ጉሃላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here