የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
22

አቶ እሱባለው ተፈራ በጸደይ ባንክ ዳሞት ቅርንጫፍ የተበደሩትን ብድር በውሉ መሰረት መመለስ ስላልቻሉ ለብድሩ መያዣ የተያዘውን ፤በመያዣ ሰጭው በአቶ ብርሃኑ ተፈራ ወርቄ ስም የተመዘገበ በፍ/ሰላም ከተማ ቀበሌ 02፣ ካርታ ቁጥር 9-111-11-2015 የሆነ፣ በሰሜን እና በምስራቅ መንገድ፣ በደቡብ ይህአለም መኮነን፣ በምእራብ ደመላሽ መኮነን፣ የሚያዋስነው የቦታው ስፋት 212.5 ካሬ ሜትር የሆነ፤ የመኖሪያ ቤት ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም፣ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 በመነሻ ዋጋ ግምቱ 5‚637‚467.37 (አምስት ሚሊዩን ስድስት መቶ ሰላሳ ሰባት ሽህ አራት መቶ ስልሳ ሰባት ብር ከሰላሳ ሰባት ሳንቲም) ይሸጣል፡፡ ስለሆነም መጫረት የምትፈልጉ ፡-

  1. የጨረታ ቦታው ፍ/ሰላም ከተማ ዋናው አደባባይ ከፍ ብሎ ከሚገኘው ጸደይ ባንክ ቅርንጫፍ ሲሆን፤ ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ወይም በጥሬ ገንዘብ ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ሲቀርቡ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቹ ድርጅት ከሆነ የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ፣ እንዲጫረት የሚፈቅድ ውክልና እና ድርጅቱ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  4. ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውንም ግብር ቫትን ጨምሮ እንዲሁም ከቦታውና ከቤቱ ዝውውር ጋር የተያያዘ ክፍያ በተጫራቾች ወይም በገዢ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  5. የጨረታው አሸናፊ ጨረታው በሚመለከተው አካል ጸድቆ አሸናፊነቱ በተረጋገጠ በ15 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ሙሉውን ገንዘብ ከፍሎ በማጠናቀቅ ቤቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡
  6. የተሻለ አማራጭ ካገኘ ባንኩ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው፡፡ ለበለጠ መረጃ 058 775 11 54 መደወል ይቻላል፡፡

የጸደይ ባንክ ፍ/ሰላም ዲስትሪክት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here